Home ዜና ከምእራብ ትግራይ ለተፈናቀሉ  የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት እርዳታ አበረከቱ፡፡

ከምእራብ ትግራይ ለተፈናቀሉ  የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት እርዳታ አበረከቱ፡፡

1151

ከምእራብ ትግራይ ተፈናቅለዉ  በመቐለ መጠለያ ካምፕ ላይ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ  በቦታዉ በመገኘት የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት እርዳታ አደረጉላቸዉ፡፡      

የሃይማኖት መሪዎች አክለዉም ይሄ አስከፊ ቀን እስኪያልፍ  የመተጋገዝ ባህላችንን በመጠበቅ ሁሉም ህብረተ-ሰብ በመተባበር የፋሲካ በዓልን ካለዉ ተከፋፍሎ  እንዲያሳልፍ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ ባለፈው ዓመት በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት በይፋ ከመጀመራቸው በፊት ጀምሮ፣ የትግራይ ሃይማኖት ተቆማት ድርጊቱ በድርድር እዲፈታ በግልና በተቋም ደረጃ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በተቃራኒዉ ደግሞ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉን ጀኖሳይድ እንዲቆምና ችግሩን በድርድር እንዲፈታ ከመስራት ይልቅ በተለያዩ መድረኮች እየተገኙ ጦርነቱን ደግፈዉ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ የፅድቅ መንገድ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ይታወቃል፡፡

የትግራይ የሃይማኖት ተቆማት ከምእራብ ትግራይ ተፈናቅለዉ በመቐለ መጠለያ ካምፕ ላይ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቦታዉ በመገኘት በፀሎታቸዉ እንደሚስቦቸዉና ከጎናቸዉ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

አሁንም የትግራይ ምእራባዊ ዞን የሚገኙ ማህብረሰብ በከባድ ችግር ዉስጥ እንደሚገኙ በመግለፅ እዚህ የተገኘነዉ እናንተን ለማፅናናትና ከጎናቹሁ እንደሆንን ለማሳየት ነዉ ሲሉ የትግራይ የሃይማኖት ተቆማት ይናገራሉ፡፡

በመላዉ ትግራይ የሚገኙ ማህበረሰቦች ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ  ላይ እየፈፀሙት የሚገኙትን ጀኖሳይድ መቆም ስላቃታቸዉ ዉድ ሂወታቸዉን ለማትረፍ በላባቸዉ ያፈሩትን ሃብት ንብረታቸዉን ጥለዉ  በተለያዩ አከባቢዎች ተፈናቅለዉ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የትግራይ የሃይማኖት ተቆማት ሀገራችን የቀድሞ ሰላሟ ተመልሶ በሰላም በእግዛብሄር እርዳታ በቅርቡ ወደየ አከባቢያቹህ  ትመለሳላቹሁ ብለዋል፡፡

 የምእራብ ትግራይ ተፈናቃዮች በበኩላቸዉ በምእራብ ትግራይ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ ለመግለፅ የሚከብድ ነዉ በማለት የሃይማኖት አባቶች  እያሳለፍነዉ ያለነዉን ችግር ተረድተዉ እዚህ ድረስ ተገኝተዉ በፀሎታቸዉ እያሰቡን እንደሆነና ከጎነናችን እንደሆኑ ስላሳዩን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡ የሃይማኖት መሪዎች አክለዉም ይሄ አስከፊ ቀን እስኪያልፍ  የመተጋገዝ ባህላችንን በመጠበቅ ሁሉም ህብረተ-ሰብ በመተባበር የፋሲካ በዓልን ካለዉ ተከፋፍሎ  እንዲያሳልፍ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡