Home ዜና ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ

ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ

3442

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ

ጠላት በደቡብ ግንባር  በግንባሩ የነበሩትን እና ከሌላ አከባቢ ያሰባሰበውን የአማራ ልዩ ሃይል ክፍለጦሮች ፣ የወሎ ፋኖና ሚልሻ ባለፉት ኣምስት ቀናት ወደፊት ሲያስጠጋቸው ከቆየ በኋላ የፌደራል መከላከያ ሃይል ኣካል የሆኑትን ስድስተኛና ስምንተኛ የእግረኛ እዞች ፣ሁለተና ፣ስድስተኛ እና ስምንተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦሮች በመጨመር በዛሬው ዕለት ነሃሴ 18/2014 ዓ/ም ከማለዳው 11፡00 ሰዓት በጩቤ በር፣ጃኖራ፣ጉባጋላ እና በያሎው ኣቅጣጫ ወደ አላማጣ፣ ባላና ብሶበር  መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀም[ል።

በዚህ ግንባር የጀመረው ጥቃት ደቡብ ትግራይ በቁጥጥር ስር ለማስገባት የቻለውን ያህል የሚገፉ ኣጋዥ ኣጥቂ ክንፉ እንጂ ዋነኛው የዘመቻው ዒላማ ከምዕራብ ትግራይና ምዕራብ ጎንደር ወደ ኣድያቦ ፣ኣስገደ እና ፀለምቲ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

ጠላት በዘመናዊው  የዓለም ታሪክ  ባልታየ መልኩ የትግራይን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ዝንተ ዓለም የማይረሳ ግፍና ስቃይ ሲያደርስበት ከቆየ በኋላ ተዳክማል፣በጦርነት መጨረስ እችላለሁኝ ብሎ ባመነበት ባሁኑ ወቅት ለተወሰነ ወራት የቆየውን ግጭት የማቆም ስምምነት በመጣስ ሲያካሂደው የቆየውን የጆኖሳይድ ጦርነት ኣጠናክሮ ለመቀጠል  ዛሬ ማለዳ የጀመረውን ጥቃት ገሃድ ኣድርጎታል።

የተከበራቹህ መላ የትግራይ ልጆች

የትግራይ ሰራዊት ጠላት ቀድሞም የሚታወቀውን የዘመቻ ዕቅዱ መነሻ በማድረግ የጀመረውን ጥቃት ካላቆመ ባስተማማኝ ደረጃ ጥቃቱን በመመከትና በመስበር ወደ ፀረ ማጥቃት በመሸጋገር የተወረረውን ሉኣላዊ የትግራይ መሬትና የተፈናቀለው ህዝባችን ወደ ቀድሞው ይዞታው ለመመለስ የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት እንዳለው  የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ለመግለፅ ይወዳል።

ለተከበራቹህ የኢትዬጵያ ህዝቦችና የፖለቲካ ሃይሎች

የትግራይ ህዝብ ሀገሬ ለሚላት ኢትዬጵያ እጅግ ውድ ዋጋ የከፈለ ጠንካራ ኢትዬጵያ እንጂ የኢትዬጵያ  ጠላት አይደለም።ይሁን እንጂ ጠላቶቻችን ራሱን ፅኑ ኢትዬጵያዊ ኣድርጎ ያምን በነበረው የትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፅሙት ያለውን ጆኖሳይድ በመቀጠል እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከበው ለረሃብ ፣ ለበሸታና ጭንቀት ከዳረጉት ቦኋላ ዛሬ ወታደራዊ ጥቃት ጀምረውበታል።ይሁንና ፍላጎታቸው በሃይል ሊያሟሉ ከቶም እንደማይችሉ ተግንዝበው ጦርነቱን እንዲያቆሙ ፣የትግራይ ህዝብ እንደ ሕዝብ የህልውናውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል ወገናዊ ድጋፋቹሁን  እንድታሳዩት የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ጥሪዉን ያቀርባል።

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

ነሓሴ 18/2014 ዓ/ም

ትግራይ ትስዕር