በፋሽኑ ዓለም እየደመቀች የመጣችውና ከትግራይ አብራክ የተገኘችው ሞዴሊስት መዓረግ ገብረመድህን /ማጊ/ ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ሸሪኮቹ ባቀጣጠሉት የጀኖሳይድ ጦርነት እጅግ የተጎዳው የትግራይን ህዝብ ለመታደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርሿዋን እንደምትወጣ አረጋገጠች፡፡
ከተወለደችበት ከአድዋ ገጠር ልዩ ስሙ ዓዲ ሓቂ ተነስታ በፋሽኑ ዓለም እየደመቀች የመጣችው ሞዴሊስት መዓርግ ገ/መድህን /ማጊ/ ከBBC ጋር በነበራት ቆይታ እንዳለችው፣ ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ሸሪኮቹ በጥቅምት ወር 2013 ዓ/ም በትግራይ ህዘብ ላይ ያወጁትን የጀኖሳይድ ጦርነት ከሦስት ወራት በኋላ ነበር የቤተሰቦቿን ድምፅ መስማት የቻለቸው።
“ያኔ ታናሽ ወንድሜ ወደ ሱዳን መሰደዱን ተነገረኝ፤ የጎረቤቶቻችን ልጆች እንደተገደሉ ሰማሁ። የቤተሰቦቼን ድምጽ በመስማቴ ደስተኛ ብሆንም ወንድሜ ራሱን ለማዳን ወደ ሱዳን እንደተሰደደ፤ ረሃብ እንዳለና ብዙ ሰው መሞቱን እናቴ ስትነግረኝ በጣም አዘንኩኝ፤ በማለት የገለጸችው መዓርግ በትግራይ ላይ የደረሰው ጉዳት ሁሌም እጅግ እንደሚያስጨንቃት ገልጻለች፡፡
በስልክ ከቤተሰብ ጋር እያወራሁ የተኩስ ድምጽ እሰማ ነበር ያለችው ሞዴሊስቷዋ እዚህ የማውቃቸው ወዳጆቼ ስለቤተሰባቸው በአጋጣሚ ከሰሙ ብዙ መርዶ ነው የሚነገራቸው” ስትልም ነው በሀዘን ስሜት ውስጥ ሆና የምትገልጸው፡፡
የቤተሰቧ ጉዳይ ብቻም ሳይሆን በአጠቃላይ በትግራይ ውስጥ እየሆነው ያለው ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸውና ሁኔታው በፋርማሲ እና በሞዴሊንግ ሥራዋ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደረባት መዓርግ በማስታወስ፣ ጦርነቱ ባስከተለባት ተጽዕኖ ምክንያት ከሥራዋን እና ከሙያዋ እንድትርቅ የተገደደችበት ወቅት እንደነበረም ገልጻለች፡፡
ነገሮችን ለማሰላሰል ጊዜ ወስዶብኛል፤ በአምላክ እርዳታ ወደ ሥራ ተመለሻለሁ እምትሏዋ ማጊ ምክንያቷዋ ስታስረዳ ደግሞ ለቤተሰቤና በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ተስፋ መሆን ካለብኝ እኔ ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ተገንዝቤያለሁ በማለት ታብራራለች፡፡
በድሃ አገራት በተለይም በአፍሪካ እና በሕንድ ውስጥ ያሉ ድሆችን ለመርዳት በማቀድ እንቅስቃሴ መጀመሯዋን የገለጸችው መዓርግ፣ የምታቀርበውን ዕርዳታ ለማስፋት ግን የትግራይ ጦርነትና በዓለማችን የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዋና ተግዳረቶች እንደሆኑባት ትገልጻለች፡፡
ሆኖም ተስፋ ባለመቁረጥ አቅሟን በማደራጀትና አጋሮችን በማስተባበር እየሰራች መሆኑን እምትናገረው ሞዴሊስት መዓርግ፣ ችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ጫማ፣ የትምህርት ቁሳቁስ፣ ምግብ እና መጠለያ በማቅረብ ተግባር መሰማረቷዋን አስረድታለች፡፡
በሞዴሊንግ ሙያዋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ እና የተለያዩ ምርቶችን ከሚያመርቱ ኩባንያዎች ጋር እየሰራች ያለችው መዓርግ ገ/መድህን /ማጊ/፣ ጫማ የሌላቸው ሴቶች መጫሚያ እንዲያገኙ የሚያግዝ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በማቋቋም በመስራት ላይ እንደምትገኝ አስታውቃለች፡፡
ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላም ወደ አሜሪካ በመጓዝ ከአንጋፋ ኩባንያዎች ጋር በፋሽንና የውበት ሞዴሊንግ ዘርፍ ስኬታማ ስራ መስራት መቻሏዋን አስታውቃለች፡፡
ወደ አሜሪካ ካቀናች በኋላ ብዙም ሳትቆይ የልጅነት ቃሏን ለመጠበቅ፣ ከሰባት ዓመት በፊት ለድሆች ጫማ የመለገስ ሥራ የጀመረች ሲሆን፣ በ2015 (እ.ኤ.አ) ደግሞ ‘ዎክ ዊዝ ሚ’ የተባለ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ በመጀመር ወደ የእኔ ጫማ የአንቺ ጫማ ነው የሚለው በመቀየር በሥራዋ ከምታገኘው ገቢ እና ከሌሎች ለጋሾች በሚገኝ ገንዘብ ጫማ በመግዛት ከትግራይ አልፋ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በማስፋት ለተቸገሩ ማድረስ እንደቻለች ገልጻለች መዓርግ፡፡
አማረ ኢታይ