Home Uncategorized የትግራይ ወታደራዊ ሰራዊት ኮማንድ መግለጫ፡፡

የትግራይ ወታደራዊ ሰራዊት ኮማንድ መግለጫ፡፡

3979

በኢትዮጵያና በትግራይ መንግስታት መካከል በሦስተኛ ወገን በኩል ለሰብአዊነት ሲባል ግጭትን የማቆም የተናጠል ውሳኔ በተደረሰው መግባባት መሰረት በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ሰራዊት መካከል ላለፉት ስድስት ወራት ወታደራዊ ግጭት ቆሞ እንደቆየ የትግራይ ህዝብ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች እና መላው የዓለም ማህበረሰብ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡

የተደረሰው ግጭትን የማቆም ውሳኔ ወደ ጦርነት ያደረሰውን ፖለቲካዊ ምክንያት ለመፍታት ወደ የሚያስችል ድርድር ለማሳደግ የአፍሪካ ህብረትና መላው የዓለም ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ  እያካሄዱት ያለውን ያላሳለሰ ጥረቶችን አጠናክሮው እየቀጠሉበት እንዳሉ ግልጽ ሆኖ ለሁሉም ጥረቶቻቸው ያለውን አድናቆት የትግራይ  ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ሳይገልጽ አያልፍም።

የትግራይ መንግስት ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም መሰረት አድርጎ በሰጠው አቅጣጫ የሰላም አማራጭ አማጥጦ እስኪያአጠናቅቅ ድረስ የትግራይ ሰራዊት ለማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ግጭት ምክንያት እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

እንዲህ ሆኖ ሳለ ነሓሴ 09/2014 ዓ/ም በምዕራብ ትግራይ የማይደፈር የብረት መከላከያ ገንብቻለሁ እያለ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደደቢት አቅጣጫ መደበኛ የመከላከል ተግባሩ እየፈጸመ ባለው የትግራይ ሰራዊት ሃይል ከሰዓት በኃላ ከቀኑ ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ሰዓት የቆየ የከባድ መሳሪያዎች እና በታንኮች የታገዘ ድብደባ አካሂዷል፡፡

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ከወገን ምንም ዓይነት የአጸፋ ምላሽ እንዳይኖር በማድረግ ይህ በግጭት የማቆም ውሳኔ ላይ የተፈፀመው ጥሰትን በአከባቢው ባለው አዛዥ የተፈጸመ ጉድለት ወይም ከላይ ሆን ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ በትአግስት ሲያጠናው ከቆየ በኃላ ድርጊቱ በበላይ አካል ታውቆ ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ምዕራብ ትግራይን የትግራይ ላለማድረግ የኢትዮጵያ መሪዎች ይዘውት ያለው የተቀናጀ ወታደራዊና እና ፖለቲካዊ ሴራ በዚህ የግጭት ማቆም ውሳኔ ጥሰት አጠናክረውታል።

ይህ ድርጊታቸው የትግራይ መንግስትም የምዕራብ ትግራይ ነጻ ማድረግ እና የተፈናቀለው ህዝባችን ወደ ቦታው መመለስ ሃይል ብቸኛ አማራጭ እንዲሆን እያደረጉ እንደሆኑ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ተገንዝቦታል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ይህ እንዲሆን የሚገፋፋው የሆነ ይሁን ግምገማ ትክክለኛ ያለሆነና አሁንም ያለው አማራጭ ሰላምና ለሰላም ቁርጠኛ መሆን ብቻ እንደሆነ እያሳሰብን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦችና የፖለቲካ ሃይሎች ፣ለመላው የኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲሁም የዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ሃገርን ወደ አውዳሚ እና ጠቅላላ ውድቀት የሚዳርግ ጦርነት ዳግም እንዲለኮስ በማድረግ ላይ ብቸኛው ተጠያቂው ቀድሞውንም በትግራይ ህዝብ ላይ የጆኖሳይድ ጦርነት ያወጀ ፣የፈጸመና እየቀጠለበት ያለው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን ሁሉም እንዲያወቀውና እንዲገነዘበው የትግራይ  ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳውቃል፡፡

ትግራይ ትስዕር !!

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

ነሓሴ 11/2014 ዓ/ም