Home ዜና ዛሬ የትግራይ ብርቅዬ ልጆች ባስመዘገቡት አኩሪ ድል ኢትዮጵያዊያን ደስታቸው በአደባባይ ሲገልፁ ተስተውለዋል።

ዛሬ የትግራይ ብርቅዬ ልጆች ባስመዘገቡት አኩሪ ድል ኢትዮጵያዊያን ደስታቸው በአደባባይ ሲገልፁ ተስተውለዋል።

571

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ የእነዚህን ጀግኖች ቤተሰቦች ጉዳይ እያሳሰባቸው ድምፃቸው ከፍ አድርጎ ማሰማት ጀምረዋል፤  ከወደ ደቡብ ትግራይ ቦራ ከተማ ደግሞ የብርቅየዋ አትሌት ጎደፋ ፀጋይ ቤተሰቦች ሀዘንና ደስታ የተቀላቀለበት ድምፃቸው ያሰማሉ።

በአስራ ስምንተኛዉ አለም አቀፍ የሻምፒዮን ውድድር የ 5000 ና የ 1500  የአትሌትክስ ዉድድር ላይ በመሳተፍ የወርቅና የብር ሜዳልያ አሸናፈዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ቤተሰቦች የልጃቸውን ደስታ መጋራት እንዳልቻሉ አስታወቁ፤ ለዚ ታሪካዉ ድል ለማክበር አልታደሉም፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖረው  ከበባና ክልከላ ምክንት  የአትሌቷ  ቤተሰቦች በከባድ ችግር ዉስጥ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

በደቡብ ትግራይ የምትገኝ የቦራ ከተማ በቀኑ የጨለመባቸው መሬቷ በንፁሃን ተጋሩ ደም የታጠበባት በፋሽስቶች የሚያሰቅቅ ጭካኔ የተፈጸመባት  ከትግራይ  ከተሞች መካከል አንዷ ነች፤ በቦራ ወረዳ በወራሪዎችና በፋሽስቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል ፣ የከተማዋ ሃብትና ንብረት ወድሟል፤ ተቃጥሎል ተዘርፏል፤ በዚቹ ከተማ ተወልዳ ደገችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተወልዳ ካደገችበት በቦራ ከተማ ነዉ፤ የተወለደችው ይህች እህታችን ደግሞ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በኢትዮጵያ ስም በክብር ከፍ ያደረገችዉን ባንዲራ የያዙ የፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ሰራዊት በቦራ ከተማ በሚኖሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ሲፈፀሙ  ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባት ሰለባ  ነች፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖሩት ከበባና ክልከላ መክንያት የ 5000 ና የ 1500 የረጅምና የአጭር የሩጫ ዉድድሮች ላይ በመሳተፍ  የአሸናፊነትን ወኔ በመሰነቅ የወርቅና የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችዉ የአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ቤተሰቦች አቶ ፀጋየ ደስታና ወ/ሮ ፅሃይነሽ ሃድሽ ጠላቶች ሳይቀሩ ደስታቸዉን ባደባባይ የገለፁበትን የዛሬዋ  ቀን   ግን ለማክበር አልታደሉም ፡፡

ለአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከቤተሰቦቿ ጋር በማለያየት የኢትዮጵያ ባንድሪ ይዛ በአለም መድረኮች ላይ እንድትወዳደር ያደረገዉ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ክብርና ጀግንነትን በመመኘት የኢትዮጵያ ባንድራ በአለም መድረክ  ከፍ ብሎ እንዲዉለበለብ ያደረገችዉና የኮራባት የአትሌት ጉዳፍ ፀጋየ መኖርያ ቤት በወራሪዎች ተዘርፏል ቤተሰቦቿንም  አዋርዷል፡፡

ከ ስድስት መቶ ቀናት በላይ ያስቆጠረዉ በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የጀኖሳይድ ጦርነት ከሞት የተረፈዉ የትግራይ ህዝብም ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ባንክ፣ ስልክ፣ መንገድና የመሳሰሉትን በመዝጋቱ  በከባድ ችግር ዉስጥ እንደሚገኝና  ባለድሏ የአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከቤተሰቦቿም እንደማንኛዉም የትግራይ ህዝብ ኑራቸዉ  በከፋ ደረጃ  እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እየተደረገ ያለው  ያለዉ ከበባና ክልከላ ተወግዷ በሰላም እስክንገናኝ የትግራይ ህዝብንና ቤተሰቦችሽን የሚያኮራ ስራ በመስራትሽ ኮርተንብሻል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል የአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ቤተሰቦች ፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ