Home ዜና የምዕራብ ትግራይ ህዝብ ሳይሸበር ለቋንቋው፣ ለማንነቱ፣ ለመሬቱና ግዛታዊ አንድነቱን ለማስመለስ እየታገለ መሆኑ...

የምዕራብ ትግራይ ህዝብ ሳይሸበር ለቋንቋው፣ ለማንነቱ፣ ለመሬቱና ግዛታዊ አንድነቱን ለማስመለስ እየታገለ መሆኑ ተነገረ፡፡

1102

የትግራይ ምእራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃነ ገብረእየሱስ ጠላት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በሰለማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጽመው አረሜናዊ ተግባር አሁኑም አጠናክሮ እንደቀጠለበት  አስታወቁ፡፡

ይሁን እንጂ ህዝቡ ሳይሸበር ለቋንቋው፣ለማንነቱ፣ለመሬቱና ግዛታዊ አንድነቱን ለማስመለስ እየታገለ ነው ተብሏል፡፡

ጠላቶች የትግራይን  ህዝብ ከምድረገጽ ለማጥፋት አልመው እንደተነሱ ላለፉት ሁለት አመታት ገደማ በመላው ትግራይ እና ከትግራይ ውጭ ባሉ አከባቢዎች የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው አረሜናዊ ተግባር ራሱ ምስክር  ነው፡፡

በተለይ በምዕራብ ትግራይ የተፈጸመው አቻ የማይገኝለት ግፍ መቼም የማይረሳ ሲሆን የፋሽስቱ አብይ ቡድን ተስፋፊው የአማራ ሃይል አሁኑም ይህንን ግፍ አጠናክረው እንደቀጠሉበት የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ብርሃነ ገብረእየሱስ እንደተናገሩት በወራሪ ሃይሎች ከቀዬቻው የተፈናቀሉ ወገኖች በተኖረው ከበባና  ክልከላ በረሃብና  በሽታ ህይወታቸውን እያጡ እና እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡

ምዕራብ ትግራይ ውስጥ የቀሩ ዜጎች በማንነታቸው ብቻ አሁኑም በጅምላ እየተገደሉ፣እየታሰሩ እና እየተሰቃዩ እንደሚገኙ፣ሴቶች ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ በአጠቃላይ ጠላቶች በህዝቡ የሚያደርሱት የጀኖሳይድ ወንጀል አጠናክረው እንደቀጠሉበት ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ምዕራብ ትግራይ ያለው ይሁን የተፈናቀለው የምዕራብ ትግራይ ህዝብ የዞኑ አስተዳደር ወደ ቦታው እንዲመለስ እንዲሁም ለህልውናው ለመሬቱና እና ለግዛታዊ አንደነቱ በጠላቶች  ሳይሸበር እየታገለ ነው ብለዋል አቶ ብርሃነ ገብረእየሱስ፡፡

ከወልቃይት ወረዳ ማይጋባ ከተማ ተፈናቅለው በሽረ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ አቶ  ብዬን በርሀ ጠላቶች በተለይ የፋኖ ቡድን በተቀናጀና በግላጭ ትግራዋይ በዚህ ምድር መኖር የለበትም መጥፋት አለበት እያሉ በግፍ  ጨፍጭፈዋል እኛ  ምስክር ነን ብለዋል፡፡

አሁኑም ግፉ እየቀጠለ ነው መረጃ ይደርሰናል ያሉት አቶ ብዬን የምዕራብ ትግራይ  ህዝብ ለህልውናው፣ለመሬቱና  ለሉአለዊነቱ እየታለ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በጽንፈኛው ፋኖ ቡድን አስከፊ ድብደባና ስቃይ የደረሰባቸው ከዳንሻ ከተማ የተፈናቀሉ አቶ አስገለ ገብረጀወርግስ በበኩላቸው ሀገርን ያቀና የትግራይን ህዝብ እንዲጠፋ  መመሪያና ትእዛዝ አስተላልፈው  ሆን ብለው የፈጸሙት የጀኖሳይድ ወንጀል ነው በማለት በትግራይ ህዝብ የጀኖሳይድ አና የክህደት ወንጀል ተፈጽሟል  ብለዋል፡፡

አክለውም የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ  አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ የምዕራብ ትግራይን መሬት በሃይል የያዙ ወራ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ ለቀው ካልወጡ መሬታችን እና ግዛታዊ አንድነታችን  ለማስመለስ እንገደዳለን ሲሉ ገለጹ፡፡

የትግራይ ህዝብ ውክልና የሌለበት የፋሽስቱ ቡድን አገልጋይ የፌደሬሽን ምክር ቤት የምዕራብ ትግራይን ጉዳይ የማየት ሆነ የመወሰን  ስልጣን የለውም ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃነ ገብረእየሱስ  መንግስት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሰፊ እድል ቢሰጥም ፣መታወቅ ያለበት ግን የምዕራብ ትግራይን መሬት ወደ ድርድር አይቀርብም ብለዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን አገልጋይ የሆነው የፌደሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ የምዕራብ ትግራይ በህገ መንግስታዊ መንገድ እንፈተዋለን ማለቱ በትግራይ ህዝብ እንደመሳለቅ  ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የትግራይ ህዝብ ውክልና  በሌለበት ሁኔታ ጉዳዩን የማየትም  ሆነ የመወሰን ስልጣን  የለውም ብለዋል፡፡

ተስፋፊዎች በሌሎች ሀይሎች ጭምር ታግዘው በጉልበት የያዙት የምዕራብ ትግራይን መሬት በሰለማዊ መንገድ ለቀው ካልወጡ መሬታችን ለማስመለስና ግዛታዊ አንድነታችን ለማስጠበቅ እንገደዳለን ነው ያሉት፡፡

ወ/ሚካኤል ገ/መድህን