የተሰው ጀግኖቻችንን ኣደራና ስእለት በጠንካራ ትግልና መከታ በተተኪ ትውልዶች እያንፀባረቀ ይኖራል! ዶ/ር ደብረፅየን
—–
የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የጀግኖች ሰማእታት አደራ ውጤታማነትና ለህዝባችን የወደፊት ልባዊ ምኞት ዛሬም እንደ ትላንቱ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ማይቀረው የድል ምእራፍ ልንገሰግስ ይገባል ሲሊ ጥሪ አቀረቡ።
የተሰው ጀግኖቻችን የተዋደቁላቸው አላማዎች ግባቸውን እንዲመቱ በማድረግ ህያውነታቸው እንደ ፀሓይ ይደምቃል።
የትግራይ ህዝብ ለሺህ ዓመታት ታሪኩን ማንነቱንና ክብሩን ጠብቆ ወደ ፊት መሄድ የቻለ እምቢ ለአምባገነንነትና ለባርነት ብሎ እንደ ህዝብ ሰምሮ ስለታገለና ወደር የለሽ መስዋእትነት ስለከፈለ ነው።
የትግራይ ህዝብ የታሪክ ምእራፎች የአሸናፊነት ታሪክ የፅናት ተምሳሌት እና ወደር የሌለው ህዝባዊነት ነው።
ዘንድሮ ሰኔ 15 ቀን ሰማእታትን ስናከብር የውስጥና የውጭ ሃይሎች የጋራ ግንባር ፈጥረው እንደ ህዝብ ሊያጠፉን የዘመቱብንን ጠላቶች ፊት ለፊት ገጥመን ፣ የትግራይ ህዝብ በተጋድሎ ታሪካዊ ውሎው ያከበተው ወርቃማ ታሪክ ዳግም እንደ ፀሓይ የሚደምቅ አስገራሚ ታሪክ በፈፀምንበት የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ማሰብ ከሃይለኛና ፈርጣማ ክንዱ ጋር ተጋፍጠህ ከመፈረካከስ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ባስመሰከረንበት ፣ ህልውናችንና ማንነታችንን ለማረጋገጥ በውስጥና በውጭ ያለው የትግራይ ህዝብ በሙሉ በተለየ ዳግም ፅናት መለያው የሆነው ህዝባዊ ሰራዊታችን ለማመን የሚከብዱ ፈተናዎችን በፅናት በመሻገር፣ ቃልና ስልት የዛሬዋቹና የቀደሙት የተሰውት ጀግኖቻችን በተግባር ያረጋገጥንበት ፣ ህዝባዊ መከታችንን ወደ መጨረሻው ውሳኝ ምዕራፍ በተሸጋገረበት የተለየ የትግል መድረክ እንዳለን መገንዘብ ይገባል።
የተሰውት ጀግኖቻችን መተኪያ የሌላትን አንዷን ህይወታቸውን የከፈሉት ወርቃማው ታሪካችን ህያውነቱ የሚረጋገጠው ከሁሉም በፊትና ከሁሉም በላይ የትግላችን መነሻ የሆኑት አለማዎቻችን ግባቸውን እንዲመቱ ስናደርግ ነው።
በተለይ ዳግም የራሳችን እድል በራሳችን የመወሰንና የትግራይን ግዛታዊ አንድነት ይሸራረፍ ሲከበር ፣ የትግራይን የህዝቦቿ ህልውናና ደህንነት ሙሉ በሙሉ ሲጠበቅም ጭምር ነው የተሰውት ጀግኖቻችን የሚካሱት።
የዚህ መድረክ ባለቤት የሆናችሁ የትግራይ ወጣቶች የጀግኖች ኣባቶቻችሁን ኣደራ ኣፅንታችሁ በመያዝ የህዝባችሁን ህልውናና ደህንነት ዋሰትና በማረጋገጥ ኣብነታዊ መስተንክሮችን በመስራት ለዘልዓለም የሚኖር ታሪክ እየፃፋችሁ ነው።
ስለሆነም ያ ሁኔታ እንደተፈጠረ የተሰው የትግራይ ጀግኖችን ቃልና ስእለት የምትፍፅሙ ታማኞች መሆናችሁን በግብር አሳይታችኋል።
የተሰው የትግራይ ጀግኖች ቃልና ስእለት ደግሞ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊና ዘላቂ ጥቅሞችና መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ፣ የትግራይና የህዝቧ ደህንነት የተደላደለ መሰረት ላይ እንዲገነባና የህዝባችንን ፍላጎት የምታሟላ ትግራይን ማረጋገጥ ነበር።
የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና መፃኢ ልባዊ ምኞት ይህ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ ለተሰው ጀግኖች ኣደራና ስእለት ውጤታማነትና ለህዝባችን የወደፊት ልባዊ ምኞት ደግሞ ዛሬም እንደ ትላንቱ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ማይቀረው የድል ምእራፍ ልንገሰግስ ይህን የተከበረ ቀን ምክንያት በማድረግ ጥሪየን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ።
የተሰው ጀግኖቻችንን ኣደራና ስእለት በጠንካራ ትግልና መከታ በተተኪ ትውልዶች እያንፀባረቀ ይኖራል!
ክብርና ሞገስ ለተሰውት ጀግኖቻችን!
ትግራይ ትስዕር!
ሰላም!