Home ዜና የትግራይ፣ የዓፋር እና የአገው ህዝቦች ትስስር

የትግራይ፣ የዓፋር እና የአገው ህዝቦች ትስስር

1563

የትግራይ፣የዓፋር እና የአገው ህዝቦች ጨቋኙን የደርግ ስርዓት ለመደምሰስ በጋራ እንደታገሉት ሁሉ አሁንምራ ስንበራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ የህዝቦች መብት እንዲሁም ታሪክና ማንነት በሃይል ለማጥፋት በሽርክና እየሰሩ ያሉትን ፋሽስታውያን እስከ መጨረሻው ለማጥፋት አድነታቸውን አጠናክረው በጋራ እንደሚታገሉ ተገለፀ፡፡

የዓፋር ፌደራሊስት ሃይሎች እና የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ በመቐለ ከተማ ባካሄዱት የውይይት መድረክ አፋር ፌደራሊስት ሃይሎች እና አገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ከትግራይ ህዝብ ጎን ተሰልፈው በሚያደርጉት የህልውና ትግል ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ተወያይተዋል፡፡

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ኪሮስ አመሃ ፋሽስታውያንና ወራሪ ሃይሎች ከሕገ መንግስታዊ ስርአቱ ውጪ የህዝቦች መብትና ነፃነትን በሃይል በማፈን ለማንበርከክ እያደረጉት ያለው ጣምራዊ እንቅስቃሴ በማምከን የትግራይ፣የዓፋር እና የአገው ህዝቦች አንድነታቸውን አጠናክረው በመታገል እንደልምዳቸው ታሪክ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የዓፋር ፌደራሊስት ሃይሎች ሊቀ መንበር ሓጂ ስዩም አወል በበኩላቸው ፋሽስታውያንና ወራሪ ሃይሎች የትግራይ፣የዓፋር እና የአገው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለመሸርሸር እያደረጉት ያለው ሴራ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የፓርቲዎቹ አመራሮች እንዲሁም ከሶስቱም ህዝቦች የተወከሉ ምሁራን እና የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡