Home ዜና የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማስጠበቅ  የትግራይ ሴቶች የአምበሳውን ደርሻ በመውሰድ ጉልህ ሚና እንደፈፀሙ...

የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማስጠበቅ  የትግራይ ሴቶች የአምበሳውን ደርሻ በመውሰድ ጉልህ ሚና እንደፈፀሙ ተገለፀ፡፡

1064

ፋሽስታውያን እና ወራሪ ሐይሎች በመመከት የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማስጠበቅ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ትግል የትግራይ ህዝብ ባስመዘገባቸው አመርቂ ድሎች የትግራይ ሴቶች የአምበሳውን ደርሻ በመውሰድ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ተገለፀ፡፡

ይህን የተገለፀው በትግራይ ሴቶች ማህበር አዘጋጅነት በመቐለ ከተማ በተካሄደው የሴቶች ኮንፈረንስ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ የትግራይ ህዝብ ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ ለማዳን በተደረገውና እየተደረገ ባለው ፍትሓዊ ትግል የትግራይ ሴቶች ሚናን በመገምገም ቀጣይ የትግል ምዕራፍ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡ 

የትግራይ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ እና የትግራይ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር ወ/ሮ አበባ ሃ/ስላሴ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ፤ አስካሁን በተደረገው ትግራይን ነፃ የማውጣትና ህልውናን የማስጠበቅ ትግል በተገኙ አመርቂ ድሎች የትግራይ ሴቶች የአምበሳውን ድርሻ በመውሰድ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ጠላትን እስከወድያኛው ለማጥፋት ከህዝባዊ ሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ድሉን ከግብ ሊያደርሱት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የውይይቱ  ተሳታፊዎች በበኩላቸው እስካሁን ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉን አቀፍ ትግል በማጠናከር ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ያኖረውን ከበባና ከልከላ እስኪ ሰበር አሁንም ከህዝባቸው፣ ከመንግስታቸውና ከሰራዊታቸው ጎን በመሰለፍ ጊዜው የሚጠይቀውን ሁሉን ዓይነት ትግል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊዎቹ ገልፀዋል፡፡