Home ዜና የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበትን አስከፊ ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ...

የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበትን አስከፊ ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ ተማሪዎች አሳሰቡ፡፡

775

—-

በሎስ አንጀለስ የካሊፈርኒያ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ ተማሪዎች   ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ግብረ አበሮቹ ባወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የትግራይ ህዝብ ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን Daily Bruin ድረ ገጽ ዘገበ፡፡

የፋሽስቱ ቡድንና ግብረ አበሮቹ የመገናኛ አውታሮችን ዘግተው በትግራይ ህዝብ ለፈጸሙት ዘግናኝ ወንጀል ሊጠየቁ እንደሚገባ ነው የቀድሞ ዬኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያሳሰቡት፡፡

Daily Bruin ድረ ገጽ በሎስ አንጀለስ የካሊፈርኒያ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ ተማሪዎችን  ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የፋሽስቱ ቡድንና ግብረ አበሮቹ የመገናኛ አውታሮችን ሆን ብሎ በመዘጋት በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጁት ጦርነት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በረሃብ አለንጋ እየተሰቃየ ነው፡፡

በጦርነቱና ጦርነቱን ባስከተለው ረሃብ፣ መሰረታዊ የመድሃኒት እጦትና ተዛማጅ ችግሮች ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን የትግራይ ሰላማዊያን ዜጎች በሞት ተቀጥፈዋል፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደግሞ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ መሆኑን የቀድሞ ተማሪዎቹ  እንደገለጹለት ድረ ገጹ ዘግቧል፡፡

በመገናኛ አውታሮች መዘጋት ምክንያትም በውጪ አገራት የሚገኙ የዩኒቨርስቲው የቀድሞ ተማሪዎች  ቤተሶቦቻቸው አሁን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

የካሊፈርኒያ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው ከተከታተሉ የቀድሞ የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራዎች መካከል ፌቨን ግርማይ አንዷ ስትሆን አያትዋን  ካገኘቻቸው ከ10 ወራት በላይ እንደሆናት ተናግራለች፡፡

በዩኒቨርስቲው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆነችው ፌቨን፣ከትግራይ አብራክ ከተገኙ ቤተሰቦች እንደተወለደችና ቤተሰቦቿ ከተወለዱባት ትግራይ ወጥተው እንደማያውቁ ብታውቅም አሁን ያሉበት ሁኔታ ለማወቅ እንደተቸገረች ትገልጻለች፡፡

የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራዎች እጣ ፈንታ ልክ እንደ ፌቨን ተመሳሳይ ነው ያለው ዘገባው፣ የፋሽስቱ ቡድንና ግብረ አበሮቹ በትግራይ በቀጠለው የጆኖሳይድ ጦርነት ምክንያት የመገናኛ አውታሮች በመቋረጣቸው አንድም የቤተሰብ አባል እንዳለገኙ የተናገሩት ደግሞ በዩኒቨርስቲው የቀድሞ የታሪክ ምሁር የሆኑት እና የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራ ዳኒኤል ሓጎስ ናቸው፡፡

ለትግራይ ህዝብ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲሰባስብ እያደረጉ ካሉ ምሁራን መካከል ዳኒኤል አንዱ ሲሆኑ፣ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ምርጫን አሳብቦ በትግራይ ህዝብ ላይ ባማወጅ ጦርነት በርካታ ጥፋቶች መፈጸማቸውን አስታውሰዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃትን በመፈጸምና ህዝቡን በማስራብ እንደ አንድ የጦር መሳሪያ ስልት እንደተጠቀሙበትም ነው የቀድሞ ተማሪዎቹ በሰጡት አስተያየት የገለጹት፡፡

የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበትን አስከፊ ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ያሉት የቀድሞ ተማሪዎቹ ፣አሜሪካም የፋሽስቱ ቡድንን ከአጎዋ ተጠቃሚነት እንዲወጣ ያደረገውን እርምጃ በማጠናከር እና HR 6600 ረቂቅ ህግን ጸድቆ ስራ ላይ እንዲውል  ድርሻዋን እንድትወጣ አሳስበዋል፡፡

አማረ ኢታይ