የትግራይ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በአፍሪካ ሕብረትም የሚመራ የሰላም ድርድርም ሆነ የህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን አባሳንጆን ኤርትራን ወደ ሰላም ድርድሩ መጋበዝ አጥብቃው ነቅፈውታል።
የፖለቲካ ቀውስን በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ለማምጣት እውን አይመስልም የጀኖሳይድ ጦርነት ሳያቋርጥ መቀጠሉን ምዕራብ ትግራይ አሁንም በጭካኔ በተስፋፊው የአማራ ሃይልና በአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት ቁጥጥር ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ በታቀደና በተቀናበረ ዘዴ የዘር ማፅዳት ወንጀል መፈፀማቸው እንደቀጠሉበት አመላክተዋል።
በውጤቱም በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የትግራይ ተወላጆች በሃይል ከቀዪአቸው እንደተፈናቀሉና የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በምስራቃዊ፣ ማእከላዊና ሰሜን ምዕራባዊ የትግራይ ዞኖች አለም አቀፍ የጦርነት ህግንና የሰብአዊ መብቶችውን በመጣስ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የፋሽስቱ የአብይ ቡድን በበኩሉ የትግራይን ህዝብ በሁለንታናዊ ከበባ ሥር እንዲወድቅ በማድረግ በህዝቡ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሎበታል ብለዋል።
ለሰብአዊነት ሲባል የተደረሰው የግጭት ማቆም ውሳኔን ተከትሎም ወደ ትግራይ የሚገባው የእርዳታ መጠን ካለው ተረጂ አንፃር በቂ እንዳልሆነ አመላክተዋል።
በነዳጅ እና በጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት እርዳታ ለጋሾች በትግራይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በእጅጉ ለመገደብ እንደተገደዱም አብራርተዋል።
ሰው ሰራሽ ቀውስ እንዲባባስ በትግራይ መሠረታዊ የማህበረ ኢኮኖሚ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ መደረጉ በፅሁፋቸው ያመለከቱት አቶ ጌታቸው የባንክ አገልግሎቱ መቋረጥ በተለይ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንና ሚልዩኖች የትግራይ ተወላጆች ጥረውግረው ያገኙቱንና የቆጠቡትን ገንዘብ መጠቀም ባለመቻላቸው ለከፍተኛ መከራ በመዳረገቸው መሠረታዊ በህይወት የመኖር መብታቸውን ተጥሷል ብለዋል። ይህም በዓለም አቀፍ ሕግ ሊጣስ የማይገባው መብት እንደሆነ አስምረውበታል።
ከእነዚህ በመሬት ላይ የሚታዩ እውነታዎች መታረቅ ያልቻለ የሰላም ሂደት ዞሮ ዞሮ መክሸፉ አይቀርም ያሉት አቶ ጌታቸው
ኦሉሴንጉን አቦሳንጆ በቅርቡ ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ ተከትሎ በትግራይ መንግስትና በፋሽስቱ ቡድን የአፍሪካ ህብረት እውን የሚሆን የዲፕሎማሲ እመርታ ይኖራል ብሎ ተስፋ ማድረጉን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው ረዳ በድርድር ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስና አጠቃላይ የፖለቲካ መፍትሄ ለመስጠት አባሳንጆ ለዚህ ቦታ ሲሸሙ ከነበረው ሁኔታ ምንም ለውጥ እንደሌለው አስረድቷል።
ከዚህ አንፃር የሕብረቱ መልካም ቀና ነገር የመጠበቅ አዝማሚያ ህብረቱ ምን ያህል ከእውነታው እንደተራራቀና ከጨለማ ሆኖ እውነታውን ለመዳሰስ እየሞከረ እንደሆነ አመላካች ነው ብለዋል።
ኦሉሴጉን አባሳንጆ በማብራሪያቸው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለሰላም ዝግጁ መሆኑን የሚያበረታታ ነው ብሎ ህብረቱ ግምገማ ማድረጉ የትግራይ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም እንዲይዝ ህብረቱ እንደሚያበረታታ ጥሪ ማቅረቡን የህብረቱ ግምገማ ምን ያህል እርስ በርሱ የሚጋጭ መሆኑን አብራርተዋል።
ህብረቱ የትግራይ መንግስት ለሰላም ድርድሩ ቁርጠኝነት ካላሳየ ታዲያ የአባሳንጆ ለአንድ ዓመት ያህል ከአዲስ አበባ – መቐለ ያደረጉት የዲፕሎማሲያዊ ምልልስ ምክንያቱ ህብረቱ ምን ነበር ብሎ ያስባል ብለው ጠይቀዋል አቶ ጌታቸው ረዳ
ህብረቱ ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች የአፍሪካ ህብረትን የአደራዳሪነት ሚና ላይ አለመስማማታቸው የሚያስብ ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ እመርታ የማይቀር ነው ብሎ ለምን መግለጫ ያወጣል ይህ ህብረቱ ብቻ የሚመልሰው ጥያቄ ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻ በሰላም ድርድሩ እንደሚሳተፍ ፈቃደኝነቱን ግልፅ ማድረጉን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው ሁሉም አፋኝ ስርዓቶች እንደሚያደርጉት ያለምንም ተጠያቂነት ለመጨማለቅ ሲፈልጉ ምዕራባውያንን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሰላም ድርድሩ እንዳይሳተፉ መንቀፉ እውነተኛው ማንነቱን አረጋግጧል ብለዋል።
ፋሽስቱ አብይ ከአፍሪካ ህብረት ጀርባ ሆኖ በመደበቅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአሜሪካ የአውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኞችን ወደ መቐለ እንዳይጓዙ መከልከሉ ለሰላም ዝግጁ አለመሆኑን እንዳይነቃበት በመፍራት እንደሆነ በአቶ ጌታቸው ረዳ ፅሁፍ ተመልክቷል።
የአፍሪካ ህብረት በዚህ ሁሉ ስራው ለሰላም ድርድሩ የማይመጥንና ብቃት የሌለው ድርጅት መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ በአፍሪካ ሪፖርት ድረ ገፅ ያሰፈሩት ፅሁፍ ያስረዳል።
በኩኖም ቀለሙ