Home ዜና የትግራይ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚጋዙት መንገደኞች ያስቀመጠው...

የትግራይ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚጋዙት መንገደኞች ያስቀመጠው ክልከላ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ ቷውቋዋል፡፡

1322

በቅርቡ ወደ መቐለ በረራ የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንግድ ባለፉት ሦስት ቀናት በወጣትነት የእድሜ ክልል ያሉትን መንገደኞች ከጉዞ እየሰረዘ መሆኑን መረጃዎች ኣመላክተዋል፡፡

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ አለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት በርካታ ወጣቶች መንግስት በሰጠው ትእዛዝ ነው በሚል ጉዟአቸው መሰረዙን ተናግረዋል፡፡

ጉዟአቸው  እንዲሰረዝ ከተደረጉ ወጣቶች መካከል ለአስቸካይ ህክምና ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ይገኙበታል፡፡

የትግራይ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ጠቁሞ በጉዳዩ ዙርያ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡