Home ዜና የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መልእክት

የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መልእክት

2459
0

የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በትግራይ ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲያበቃና አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ እርምጃ ካልተወሰደ የትግራይ ህዝብ በርሃብና በመድሐኒት እጦት እንዲያልቅ አንፈቅድም ሲሉ አስገነዘቡ።

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ለተባባሩት መንግስታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በላኩት ግልጽ ደብዳቤ፣ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ  ባኖሩት ከበባና ክልከላ ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠር የትግራይን ህዝብ በሰው ሰራሽ ረሃብ እያለቀ ነው ብለዋል፡፡

የዓለም ማህበረ-ሰብ አብይ የገባውን ውሳኔ እንዲፈጽም ግፊት ከማድረግ ተቆጥቧል፤ ከዚህ ይልቅ 6 በመቶ ብቻ የሚሸፍነውን እርዳታ ሲገባ አድናቆት መቸሩን መግለጽ መርጣል፡፡ አብይ ባዶ ተስፋ መስጠት ቀጥሎባታል፤ የዓለም ማህበረ-ሰብ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እየሞተ መመልከቱን ቀጥሎበታል፤  የትግራይ ሰራዊት ባለፈው ህዳር ወር ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ አጎራባች ክልሎች መውጣቱን ብቻ የሚፈለገው ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣል የሚል የአለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብ የተሳሳተ ግምት መያዙን ያስታወሱት የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤

የትግራይ መንግሰት የእለት ደራሽ እርዳታን ወደ ተጎጂዎች እንዲደርስ የማሳለጥ ስራን ለማሳካት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ሁሌም ቁርጠኝነቱን አሳይቷል ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን  በሚሊዮኖቸ ለሚቆጠር የትግራይ ህዘብ ብቻ ሳይሆን ችግር ላይ ለሚገኙ የአጎራባች ክልል ህዝቦች እርዳታው እንዲደርስም ተንቀሳቅሷል ብለዋል፡፡ የትግራይ ሰራዊት በቅርቡ ከዓፋር ኢሬፕቲ መውጣትም  የዚሁ በመርህ ላይ የተመሰረተ  እርምጃ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአለም-አቀፍ ማህበረ-ሰብ ይህንኑ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የታየውን ትንሽ የሰላም ጭላንችልን ከማዳበርና  በፋሽስቱ የአብይ ቡድንና የቀጠናው ግበረ-አበሮቹ ላይ ጫና ከመፍጠር ይልቅ አለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብና ተጸእኖ ፈጣሪ ተዋንያን የሰብአዊነት ጉዳይን ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር ሲያስተሳስሩት ታይተዋል ብለዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ተስፋፊዎቹ የአማራ ሃይሎችና የአምባገነኑ ኢሳያስ ወታደሮች በርካታ የትግራይ አከባቢዎች ወረው ይዘዋል፡፡ ይህ ግልጽ እያለ የትግራይ ሰራዊት ከዓፋር አከባቢዎች አንዲወጣ ተደጋጋሚ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ሚዛናዊነት የጎደለው ፍርድ፤ ያልተለመዱ እና መሰረታዊ እሴትን የጣሱ እርምጃዎችን ሲወስዱ፤ የትግራይ መንግስት ያለውን  ጦርነት ለሰላም ያለውን ዝግጁነት አሳይቷል ብለዋል

በመርህ ደረጃ ከሁሉም የዓፋር አከባቢዎች ለመውጣት ዝግጁ ነን፡፡ የዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብና የአብይ መንግስትም ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች አሉ፡፡

ዶክተር ደብረጽዮን በተፈጠረው ቀውስ፣  አንድነት የሚጎዳና ብዙዎችን እያስለቀሰ ባለው   ኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚየዊና ፖለቲካዊ ችግር ላይ ወድቃለች፤ ለአዲስ ትውልድ የሚተርፍ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች ብለዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ እልቂት እና ስቃይ እንዲሁም የሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት የትግራይ መንግስትና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለሰብአዊነት ሲባል ጊዝያዊ ግጭትን የማቆም ውሳኔ በተናጠል መደረሱን ያስታወሱት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ይሁን እንጂ ውሳኔው በአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ አዎንታዊ ምላሽ እንዳልተሰጠው  አስታውቀዋል፡፡

ውሳኔን ተግባራዊ አንዲደረግ የትግራይ መንግስት ሰራዊቱን ተቆጣጥሮት ከነበረው የዓፋር ክልል ኤሬፕቲ አከባቢ በገዛ ፈቃዱ መውጣቱን ዶ/ር ደብረጽዮን በማስታወስ ሆኖም በአብይ ቡድን በኩል የተወሰደው አርምጃ ግን የጀብደኝነትና ምላሽ ነው ብለዋል፡፡    

ለትግራይ ህዝብ የሰብአዊ እርዳታ በቂ ሁኔታና በወቅቱ ማቅረብ እንደ ችሮታ ሊታይ አይገባውም ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ የትግራይ መንግስትና ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አስከፊ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ባለበት ሁኔታ ሰብአዊ እርደታን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም የሚደረገው ክልከላ ከሰብአዊነት የራቀ ተግባር ነው ብለውታል፡፡

በመሆኑም ይላሉ ዶ/ር ደብረጽዮን በደብዳቤያቸው፦ ለትግራይ ህዝብ የሰብአዊ እርዳታን በወቅቱ በበቂ ሁኔታና ያለምንም ገደብ እንዲዳረስ ለማድረግ የእርዳታ መግቢያ ኮሪዶሮችን ክፍት መደረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

እንዲሁም በትግራይ ህዝብ ያለውን ከበባ እና ክልካላ ተወግዶ መሰረታዊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ አለባቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፦ የተደረሱትን የተናጠል ውሳኔዎች ተፈጻሚ ስለመሆናቸውንም በገለልተኛ የዓለም አቀፍ አካላት ክትትል እንዲረግባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡

ትግራይን ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ሲባል የትግራይ መንግስትና ህዝብ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥና የሃገሪቱን ሉዓላዊነት እንዲከበር ግን የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በሃይል ከያዛቸው የትግራይ አከባቢዎችና ከኢትዮጵያ ምድር ያለ ቅድመ ሁኔታ መውጣት አለበት ብለዋል፡፡

አሳዛኙ ጥረታችንን  ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲገኝ ነው ያሉት  ፕሬዚዳንቱ፤ የሰላም መንገድ አማራጭ ከተዘጋ ግን የአብይ ቡድንና ግብረአበሮቹ ያኖሩት እና ትግራይን ወደ ሲኦል ምድር የቀየረው ከበባ እና ክልከላ በሃይል ለመስበር እንገደዳለን ሲሉም ነው ዶ/ር ደብረጽዮን አስገንዝበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በበርካታ ቀውሶች እየታመሰች ትገኛለች ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን በተለይ የፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ ዋነኛው ቀውስ በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

የትግራይ ሰራዊት ከተቆጣጠረባቸው የዓፋር አከባቢዎች በገዛ ፈቃዱ ለቆ መውጣቱን ለኢትዮያ ዘላቂ ሰላምና ደህነነት መረጋገጥ በቂ ማሳያ ነው በማለት ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ በአብይ ባለስልጣናትና ግብረአበሮቹ የሚታየው ጤናማ ያልሆነ ውሳኔ እና ጀብደኝነት  ግን ኢትዮጵያን ሊያጠፋት ነው ብለዋል፡፡ አሁን ያለው ችግር በአስቸኳይ ካልተፈታ የሃገሪቱ መበታተን እውን እየሆነ እንደሚመጣም አስገንዝበዋል፡፡

ወደ ትግራይ ከህዳር ጀምሮ እስክ መጋቢት መጨረሻ ወር ድረስ  በአራት ወራት ውስጥ ወደ ትግራይ 67 የጭነት ተሽከርካሪዎች ብቻ ናቸው   የገቡት ያሉት ፕረዚዳንቱ

ሰብአዊ ቀውሱ መሰረታዊ የሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ምላሽ አልሰጠም፡፡ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተዘግቷል፡፡ መሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት አጋጥሟል፤ የባንክና የትራንስፖርት አገልግሎት የለም፡፡ ለዓመታት የትግራይ ተወላጆች ለፍተው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ማግኘት አልቻሉም፡፡ በውጭ የሚገኙ የትግራይ #ዲያስፖራዎች ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ መላክ አልቻሉም፣ በዚህም ተጋሩ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡  በአጠቃላይ ተጋሩ ችግር ላይ ናቸው፡፡

ሁሉ ከበባና ክልከላ የትግራይ ተወላጆችን  ራሃብን አንደ አንድ የጦር መሳሪያ መጠቀም አላማን የመሳካት ስልት ሲሆን፣ ይህም የጦር ወንጀል ነው ሲሉም ነው የገለጹት፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ጭምር በማለት፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ይህን መሰል ግፍ እየተፈጸመባቸው እና እየደረሰባቸው ዝም ብሎ በትአግስት ሊቀጥሉ እና ሊቋቋሙት አይቻላቸውም ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

በጦርነቱና ከበባው ምክንያት በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በተጨማሪም በጅምላዊ ግድያ በመሰረታዊ መድሃኒት እጦት እና በረሃብ ተመሳሳይ የሞት እጣ የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች   በርካታ ናቸው ብለዋል፡፡

ለሰብአዊነት ሲባል በተናጠል የተደረሰው ግጭትን የማስቆም ውሳኔም ባለመተግበሩ አሁንም ሞቱ አንደቀጠለ ነው ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የተቻላቸውን  ሁሉ  አውድመዋል፣ የንብረት ዝርፊያ እና ሌሎች ወንጀሎችም ፈጽመዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የትግራይ አርሶ አደሮች አሁን ማዳበሪያ ካላገኙ ለመጭው ዓመት የሚሆን ምግብ ማምረት አይቻላቸውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፦

በሁሉም ኢትየጵያዊያን ላይ በየቦታው ጦርነት እየተካሄደባቸው ነው፣ የፌደራል መንግስቱ ህግና ስርዓትን ማስከበር አልቻለም፣ እንዲሁም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለማህበራዊ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አቅቶታል፤ በመሆኑም አገሪቷዋ ህልውና እየተናደ ነው ሲሉም ነው ያብራሩት፡፡

የኤርትራ መንግስት በሃገሪቷ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጣልቃ መግባት ምክንያት ችግር ተፈጥሯል ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ የኤርትራ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ግዛት እና ከኢትዮጵያ ጠቅልለው መውጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

አብይ ለሰብአዊነት ሲባል የገባውን ጊዝያዊ ግጭትን የማቆም ውሳኔን ተግባራዊ እንዲያደርግ ዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብና ታዋቂ ግለሰቦች ጫና ሊያደርጉበት እንደሚገባም ነው ጥሪያቸውን ያስተላለፉት ፕሬዚዳንቱ፡፡

Previous articleበትግራይ ባለፈው አመት ርሃብ ወደ 2000 የሚጠጉ ከ5 ዓመት በታች ዕድሜ የሆናቸው ህፃናት ህይወትን መቅጠፉ AP አመለከተ፡፡
Next articleከምእራብ ትግራይ ለተፈናቀሉ  የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት እርዳታ አበረከቱ፡፡