Home ዜና የትግራይ ተወላጆች በመረሸን ገድሎ በጅምላ በመቅበርና ሌሎችም   እጅግ ሙቀታማ በሆኑ የዓፋር በረሃዎች...

የትግራይ ተወላጆች በመረሸን ገድሎ በጅምላ በመቅበርና ሌሎችም   እጅግ ሙቀታማ በሆኑ የዓፋር በረሃዎች እያሰቃየ ያለው የአወል አርባ ቡድን የራሱ ቤተሰብ አባላትም መረሸኑ ተጋለጠ።

888

—-

ከስዑዲ ዓረብ ተመላሽ የትግራይ ተወላጆች ገድሎ በጅምላ መቃብር ሌሎችም ደግሞ እጅግ ሙቀታማ በሆኑ የዓፋር በረሃዎች እያሰቃየ ያለው የአወል አርባ ቡድን የቤተሰብ አባላትም መረሸኑ ተገለፀ።

የዓፋር ህዝብ ዛሬ ለራሱ ህልውና ሲል በዓፋር ምድር ስቃይ ውስጥ ያሉትን የትግራይ ወገኖች ድምፁን ማሰማት እንደሚገባ የተላላኪ ቡድኑ ቁንጮ አወል አርባ የቤተሰብ አባል የሆነው ፖለቲከኛ መንጌላ ዊትካ ገልጿል።

ፖለቲከኛ መንጌላ ዊትካ የአባቱ ታናሽ ወንድም በሆነው የፋሽስቱ ቡድን ተላላኪ የዓፋር ክልል አመራር ቁንጮ አወል አርባ ወላጅ አባቱ ጨምሮ ስድስት የቤተሰቡ አባላት በጭካኔ ቀጥፏል የአጎትየው አወል አርባ ጭካኔ በዚህ ሳያበቃ ለተላላኪነቱ አልመች ያሉትን የገዛ ወገኖቹ ማጎሪያ ካምፕ አጐሮዋቸዋል።

ታዲያ ለወንድሞቹ ያልራራው የጭካኔ ጥግ የተላበሰው ስብስብ የአወል አርባ ቡድን የትግራይ ተወላጆች በማንነታቸው ገድሎ በጅምላ መቃብር በአጋጣሚ የተረፍትም እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሙቀታማ የዓፋር በረሃዎች አስሮ እያሰቃየ ይገኛል።

ፖለቲከኛው መንጌላ ዊትካ የዓፋር ህዝብ በተለያዩ አካባቢ በማንተታቸው የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች ይፈቱ የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን በመግለፅ ህዝቡ ለወገኑም ቢሆን የማይራራውና ተላላኪ የአወል አርባ ቡድንን መቃውም ይገባዋል ብሏል።

የትግራይ መንግስት በሰሞኑ መግለጫው ከ10,000 በላይ የትግራይ ተወላጆች ዛሬም በሰመራና ሌሎች ከ40 ሴንቲግሬድ በላይ ሙቀት ባለባቸው የዓፋር በረሃዎች በስቃይ ላይ እንደሚገኙ መግለፁን ይታዋሳል።

ሄለን ወ/ዮሃንስ

መንጌላ ዊትካ