Home ዜና የትግራይ እናቶችና ሴቶች ባለፉት ግዜያት  የትግራይ መሬት የደፈሩና  ጀኖሳይድ ወንጀልን የፈፀሙ ጠላቶች...

የትግራይ እናቶችና ሴቶች ባለፉት ግዜያት  የትግራይ መሬት የደፈሩና  ጀኖሳይድ ወንጀልን የፈፀሙ ጠላቶች ግንባር ድረስ በመዝመት ተታግለዋል፣ ልጆቻቸውን መርቀው ለመስዋእትነት በመላክ  ደጀንና ግንባር በማጠናከር ለሰራዊቱ ደጀን በመሆንና የአካባቢዎቻቸው ፀጥታ በማስጠበቅ ከወንዶች እኩል የሆነ ታሪክ የማይሽረው በደማቅ ወርቅ ቀለም ተፅፎ ለዘላለም ሲነሳ የሚኖር ታሪክ እየሰሩ መጥቷል፡፡

1161

አሁንም የዚህ ተቀጥያ ጠላቶች ከትግራይ መሬት ተጠራረገው እስኪወጡና ከበባውና ክልከላው እስኪሰበር ትግላቸው በማጠናከር በታላቅ ጀግንነት በየመድረኩ እያስመሰከሩ ናቸው፡፡

ፋሽስታውያን እና ወራሪ ሐይሎች በመመከት ትግራይን ከጀኖሳይድ ጦርነት ለማናገፍና ህልውናን ለማስጠበቅ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ትግል የትግራይ ህዝብ ባስመዘገባቸው አመርቂ ድሎች የትግራይ ሴቶች የአምበሳውን ድርሻ በመውሰድ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው በተደረገው የሴቶች ኮንፈረንስ ተገልጿል፡፡

በውይይት መድረኩም የትግራይ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን የትግራይ ሴቶች የሚቻል የማይመስለውን አስቸጋሪው ሁኔታ በማለፍ እና ለዓላማ በመታገል ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለትግራይ ህዝብ መብትና ህልውና ልጆቻችሁን ግምባር ድረስ ከመላክ እስከ ደጀንና ግንባር በመሆን ከፍተኛ ዋጋ ከፍላቹሃል እየከፈላቹህም ይገኛል፤ ያሉት ወ/ሮ ሊያ ካሳ እሰካሁን ያደረጋቹህትን ትግል ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው ነው በማለት ትግሉን ዳር በማድረስ ትግራይን ከወራሪዎች ነፃ ለማውጣት እስከ መጨረሻው ትግላቸውን ማጠናከር አንዳለባቸውም አክለዋል፡፡

የትግራይ ሴቶች ማህበር ሊቀ-መንበር ወ/ሮ አበባ ሃ/ስላሴ በበኩላቸው ጠላቶች በትግራይ ህዝብ ላይ በተለይ በትግራይ ሴቶች ላይ የፈፀሙት ግፍ ለዓለም በማጋለጥ ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ በርትተው ትግላቸው ማጠናከር እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የተሳተፉ ሴቶች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ሲያደርጉት የነበረውን ትግል በማጠናከር ትግራይ ከጠላት ነፃ እስክትወጣና ከበባና ክልከላ እሰኪሰበርና  ጀኖሳይድ ፈፃሚዎች ፍርዳቸው እስኪያገኙ ሁልን ዓይነት ትግል በማጠናከር ከመንግስትና ከሰራዊታቸው ጎን እንደሚቆሙም አረጋግጠዋል፡፡