Home ዜና የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት...

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት ለስድስት ኤዺስ ቆዸሳት ሢመት ሰጠች።

462

ባለፈው ሳምንት ከተመረጡ 10 ኤጲስ ቆጶሳት ስድሰቱ ብፁአን አባቶች በርእሰ ኣድባራት ወገዳማት ኣክሱም ጽዮን ሢመት እና አንብሮተ ዕድ ተከናውነዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የታጀበው በቅድስት እና ታሪካዊትዋ ከተማ አክሱም የተከናወነው ሢመትና አንብሮተ ዕድ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት ለመጀመርያ ግዜ ያከናወነችው ነው።

፩.ብፁእ ኣቡነ ሊባኖስ – የደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ሃገረሰብከት ኤጲስቆጶስ

፪.ብፁእ ኣቡነ ናትናኤል- የምዕራብ ትግራይ ሑሞራ ሃገረስብከት ኤጲስቆጶስ

፫.ብፁእ ኣቡነ ኣረጋዊ- የከፍተኛ ቤት ክህነት መንበረ ሰላማ ከሣቴብርሃን ቤተ ክርስትያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትግራይ ኤጲስቆጶስና ዋና ፀሓፊ

፬.ብፁእ ኣቡነ የውሃንስ- የቅዱስ ፍሬመናጦስ አቡነ ሰላማ ከሣቴብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅና የመቐለ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ኤጲስቆጶስ፭.ብፁእ ኣቡነ ኣትናቴዎስ- የቨርጂኒያ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃገረስብከት ኤጲስቆጶስ

፮.ብፁእ ኣቡነ እምባቆም- የደቡብ ምስራቅ ትግራይ ኤጲስቆጶስ በማለት ተሰይሟል።

የተሾሙት ብፁአን አባቶች 5ቱ በሀገር ውስጥ ማለትም ትግራይ ውሰጥ የሚያገለግሉ ሲሆን አንዱ ብፁእ አባት ከሀገር ውጪ ማለትም በአሜሪካ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ተብሏል።

ሄለን ወልደዮሐንስ