—-
የትግራይ ህዝብ ህልውና እና ደህንነት ሙሉ በሙሉ እስከሚረጋገጥ በተለያዩ ክፍለ አለማት የሚገኙ የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረሰብ 3ኛው ዙር የመመከት ዘመቻ አጠናክረው እንደቀጠሉበት ተገለፀ፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን እና ግብረ አበሮቹ የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ይሁን እንጂ ለፋሽስታውያን እና ለወራሪ ሀይሎች እጁን የማይሰጥ የትግራይ ህዝብ ከወትሮ በበለጠ አንድነቱን አጠናክሮ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ያሴረውን ሴራ ለማክሸፍ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡
በአውሮፓ የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረ-ሰብም በሲውድን ስቶልክሆም ተሰባስበው ፌስቲቫል በማካሄድ በ3ኛው ዙር የመመከት ዘመቻ ላይ የላቀ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
በአውሮፓ የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ፌስቲቫል ማካሄዳቸው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ሸሪኮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄዱት ያሉትን የጆኖሳይድ ወንጀል ተደራጅቶው ለማጋለጥ እና ዳግም ትግራይ ለመገንባት የበኩላችን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያግዘናል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በእንግሊዝ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረሰብም በለንደን ከተማ ደማቅ ፌስቲቫል በማዘጋጀት ገቢውን ሙሉ በሙሉ ለ3ኛው ዙር የመመከት ዘመቻ የሚውል ገንዘብ አሰባስበዋል፡፡
በሱዳን የሚኖሩ ሴት የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረሰብ በበኩላቸው የትግራይ ህዝብ እየተፈፀመበት ያለውን የጆኖሳይድ ውንጀል በመመከት ዙርያ እያደረገው ያለውን ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለፅ ትግራይ ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ እስከምትወጣ ድረስ ትግላቸው አጠናክረው እንደሚቀጡልበት ገልፀዋል፡፡
በሱዳን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በ2ኛው እና በ3ኛው የመመከት ዘመቻ ላይ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሱዳን ፓውንድ ማሰባሰባቸውን በሱዳን የትግራይ ማህበር ሊቀመንበር አቶ መብራህቶም ገ/ሄር ተናግረዋል፡፡
በአውሮፓ በአሜሪካ እንዲሁም በተለያዩ ክፍለ አለማት የሚኖሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች እያካሄዱት ያለውን ፌስቲቫልና የተለያዩ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ገቢዉ ለትግራይ ሶስተኛዉ ዙር የመመከት ዘመቻ ይውላል፡፡
መአዲ ሀይለ