የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በትግራይና በህዝቡ እየፈፀመው ያለው ወንጀል በአፋጣኝ ሊታረም ይገባል ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ጠቅሷል፡፡በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረ ገፁ ላይ የትግራይ ወረዳዎች ወደ አማራ ክልል በማካለል ባሳለፍነው ወር በተመሳሳይ በትምህርት ሚኒስቴር የተፈፀመ ወንጀል በተጠናከረ መልኩ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ፈፅሟል ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
ፅህፈት ቤቱ የወሰደው ሐላፊነት የጎደለው እርምጃ የተጀመረውን የሰላም ሂደት የሚያውክና በምንም ዓይነት መለኪያ ተቀበይነት የለሌው ተግባር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊያርመውና ለትግራይ ህዝብም በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሲል ግዚያዊ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡
የፌደራል መንግስትም ቢሆን በጤና ሚኒስቴር አመራሮች አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድና ሆን ተብሎ በትምህርት ሚኒስቴርና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በተከታታይ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል በአፋጣኝ ማረም እንዳለበትም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ጥሪውን አሳስቧል፡፡