Home ዜና የአሉላ አባ ነጋ ዘመቻ የትግራይ ሰራዊት ከህልውና ጥያቄ ወደ ከፍተኛ የመፈፀም አቅም...

የአሉላ አባ ነጋ ዘመቻ የትግራይ ሰራዊት ከህልውና ጥያቄ ወደ ከፍተኛ የመፈፀም አቅም የተሸጋገረበት ዘመቻ መሆኑ  አመራሮች ገለፁ።

1150

የትግራይ ህዝብ ስምንት የሲኦል ወራትን አሳልፏል፡፡ ህዝቡ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አልመዉ  በፊስካ ተጠራርተዉ የመጡት ወራሪዎችና ፋሽስታዉያን  ከፀሃይ በታቸ የቻሉትን ሁሉ የግፍ ፅዋ በንፁሃን የትግራይ ዜጎች ላይ አፍስሰዋል፡፡ የህዝቡን ስቃይና መከራ መስማት ያማረረዉ የትግራይ ሰራዊት ታድያ እነዚህ የትግራይ ህዝብ ደመኞች  ከትግራይ ምድር ነቅሎ ለማሰወጣት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ አንደ ትልቅ ዘመቻ በጀግናዉ  የአፍሪካ የመጀመሪያዉ ጀነራል አሉላ አባነጋ ስም ሰየሙ፡፡

የትግራይ ሰራዊት ከላይ እሰከታች የህዝቡን ስቃይ ለማሳጠር ለዘመቻዉ በትልቅ ወኔና ደስታ ዝግጁ ሆነ ፡፡

ሰኔ 11. 2013 ዓ/ም የአሉላ አባ ነጋ ዘመቻ ተጀመረ፤  ሸዉዓተ ህጉም እስከ የጭላ በነበረዉና አብይ አህመድ በሚመካበት አስራ አንደኛ ክፍለ ጦር ላይ የትግራይ ሰራዊት ክንዱን ማሳረፍ ጀመረ፤ በሌሎች የትግራይ አከባቢዎች ዘመቻዉ አጣጥፎ ቀጠለ፡፡

ፋሽስቱ የሚመካበት አስራ አንደኛ ክፍለ ጦር ከትግራይ ሰራዊት ጋር ያደረገዉ ዉጊያ  ከሁለት ቀን በላይ አልቆየም አስራ አንደኛ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ በርካታ የአብይ አህመድ ወታደሮችም  በተራራዉ ላይ ረገፉ፡፡ ከአንደ ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ እጃቸዉን ለትግራይ ሰራዊተ ሰጡ፡፡

የትግራይ ሰራዊት ቁጥሩ አናሳ ነዉና እነሱን እረግጠን ደምስሰን እናልፋለን የሚል ነበረ፤ የሆነዉ ግን ሌላ ነዉ በዉጊያዉ ስልት ጥርሳቸዉን የነቀሉ የትግራይ ጀነራሎች ይህ እንኳን ገድለህ ቆጥረህም የማይጨረስ ሰራዊት እንዴት መደምሰስ እንዳለባቸዉ መከሩ፤ የህዝቡን ስቃይ ለማሳጠር በከፍተኛ ጉጉት እየተዋደቁ ያሉት የትግራይ ሰራዊትም ቦታዉን ያዘ፤ በአሉላ አባ ነጋ የተሰየመዉ ዘመቻ  በትግራይ ሰራዊት ድል ተጠናቀቀ፡፡

የትግራይ ሰራዊት ከጠላት በርካታ የጦር መሳርያዎቸን ሲማርክ በአከባቢው እንደለመዱት ከትግራይ ተዘርፎ ሊሄድ የነበረዉ ንብረትም ሙሉ በሙሉ አትርፎታል፡፡ የአብይ ወታደሮች ከአምስት ሺ በላይ የተማረኩበት ወቅት ነበር፡፡