41 ንጹሃን የትግራይ ተወላጆችን የገደለና 35 ሴቶች የደፈረ የአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ሰላይ ዳግም ጀኖሳይድ ለመፈጸም እረኛ መስሎ ወደ ትግራይ ለመግባት ሲሞክር በትግራይ ሰራዊት መማረኩን ገለጸ፡፡
ሌላኛው ምርኮኛ የአምባገነኑ ሰላይ በትግራይ ማይ ዓይኒ እና #ሕጻጽ ተጠልለው የነበሩ የኤርትራ ተወላጆች እንዲበታተኑ እና ታፍነው እንዲወሰዱ ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ሰመረ ገብረሂወት ይባላል የአምባገነኑ ኢሳያስ የ23ኛው ክፍለ ጦር የስለላ አባል ነው፡፡
በ2013 ዓ.ም የአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ሰራዊት ትግራይን በወረረበት ጊዜ በወረራው ከተሳተፉ ወታደሮች መካከል አንዱ ነው፡፡
ሰመረ በሽራሮ በኩል ወደ ትግራይ ገብቶ ህጻን ሽማግሌ ሳይል የትግራይ ተወላጆችን በግፍ ገድሏል ሴቶችን ደፍሯል፡፡
ከሽራሮ እስከ አዲ ግራት በቆየባቸው ጊዝያትም 41 ንጹሃን ዜጎች ገድሏል፤ 35 ሴቶች ደፍሯል፡፡
ሰመረ ይህን ሁሉ ግፍ ፈጽመው ግን ምንም አይነት የጸጸት ስሜት አይሰማውም ይልቁንም እንስሳዊ ባህሪ የተላበሰ ሰላይ መሆኑን ንግግሩን ያሳብቃል፡፡
ሰው መግደል ሴቶችን መድፈር ለአምባገነኑ ቅጥረኛ ሰራዊት የተለመደ ተግባር መሆኑንም ሰላዩ በአንደበቱ ይናገራል፡፡
ይህም ፋሽስቱ ኢሳያስ ሰራዊቱን ምን ያህል ሰይጣናዊ ባህሪ እንዲላበስ አድርጎ እንዳነፀው ማሳያ ነው፡፡
ታድያ የፈፀመውን ይህን ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎት ዳግም ንጹሃንን ለመግደል ሴቶችን ለመድፈር እረኛ መስሎ ወደ ትግራይ ለመግባት ሲሞክር በጀግናው የትግራይ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ሌላኛው የአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ሰላይ ገብሩ አልአዛር ትግራይ ላይ አስር ሰላማውያን ዜጎችን መግደሉንና በትግራይ በሕጻጽ እና ማይ ዓይኒ ተጠልለው የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ተኩስ በመክፈት እንዲበታተኑና የቀሩትን ደግሞ ታፍነው ወደ ኤርትራ እንዲወሰዱ ማድረጉን በአንደበቱ መስክሯል፡፡
አሁንም የአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ሰራዊት ተጨማሪ የትግራይን መሬት ለመውረር በትግራይ መሬት ምሽግ እየቆፈረ ነው ያለው ሰላዩ፡፡ ይህም የኤርትራ ወጣት ከማስጨረስ ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም ብሏል፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ በርካታ ግፍ ፈጽሚያለሁ ነገር ግን የትግራይ ህዝብ እንደ በደሌ ሳይሆን ተቀብሎ አስተናግዶኛል ያለው ሰላዩ ምርኮኛ፡፡ የኤርትራ ህዝብ አሁን መዘጋጀት ያለበት ለጦርነት ሳይሆን ለሰላም እና ለይቅርታ መሆን አለበት ይላል፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ሰራዊት ሰሙኑን ተጨማሪ የትግራይ መሬት ለመውረር በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በወሰደው የመከላከልና የጸረ-ማጥቃት እርምጃ ጠላት ከፍተኛ ሽንፈት ተከናንቦ ወደ መጣበት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
በይብራህ እምባየ