የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ በሰው ህይወት፣ ሃብትና ንብረት ከባድ ጉዳይ እያደረሰ መሆኑንና የአከባቢው ማህበረ-ሰብም እየተፈናቀለ መሆኑን ከቀዬያቸው ተፈነቅለው በሸራሮ ከተማ የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡
የአምባገነኑ ሰራዊት በትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የሚፈጽመው ግፍ አጠናክሮ እንደቀጠለበት እና በ2014 ዓም ብቻ ከ50 በላይ እረኞች ማፈኑን እንዲሁም ከ250 ሺህ በላይ የቤት እንስሳ መዝረፉን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ጽንፈኛው ፋኖ የፋሽስቱ አብይ ቡድን እና የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ በነበሩበት ወቅት በሰላማዊ ዜጎች ግፍና ጭፍጨፋ መፈጸማቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ በእነዚህ ሃይሎች በተለይ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ብቻ ከ250 በላይ ሰለማዊ ዜጎች በግፍ መገደላቸውን እንዲሁም በቢሊዮን ብር የሚገመት ሃብትና ንብረት መውደሙንና መዘረፉን ከወረዳው የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በወረዳው ከዓዲ ጸጸር ቀበሌ ተፈናቅላ በሸራሮ ከተማ የምትገኘው ወጣት ማሾ ተክላይ የግፉ ሰለባ ከሆኑት ወገኖች አንዷ ናት፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያሰ ሰራዊት ትግራይን ከወረረበት አንስቶ ያደረሰው ግፍና መከራ አልበቃ ብሎት አሁኑም በሰለማዊ ዜጎች ላይ ግፍና በደል እየፈጸመ ይገኛል ሲሉ በአምባገነኑ ሰራዊት ከቀያቸወ ተፈናቅለው ሸራሮ ከተማ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በየጊዜው እረኞች አፍኖ እንደሚወስድ እና በየቀኑ የቤት እንስሳ ዘርፎ እንደሚወስድ የገለጹት አርሶ አደሮቹ ልጆቻቸውና ከብቶቻቸው እንደተወሰዱባቸው አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል፡፡
የታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብረህይወት ገብረመድህን በበኩላቸው ባድመ ከተማ የባድመ ገጠር ቀበሌ ገምሃሎ፣ ዓዲ ጸጸር፣ አደመይቲ እንዲሁም ዓዲ አሰር የተባሉ የትግራይ ቀበሌዎች እስካሁን በአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት ስር መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
በእነዙህ ቀበሌዎች እና ሌሎች አከባቢዎች ጭምር የአምባገነኑ ሰራዊት አስከፊ ግፍ እና ትንኮሳ እየፈጸመ ይገኛል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አሁንም ድረስ በሰው ህይወት፣ ሃብትና ንብረት ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በሃይል ከያዘው መሬታችን ለቆ እንዲወጣ በተደጋጋሚ አሳስበናል፣የአለም ማህበረ-ሰብም ሊያውቅልን ይገባል የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው ካልሆነ ግን ህዘባችንና መሬታችን ነጻ እናወጣለን ብለዋል፡፡
አምባገነኑ ኢሳያስ በአሁኑ ሰአት ሰራዊቱን ወደ ትግራይ እያስጠጋ እንደሆነም እየተገለጸ ነው፡፡
ወ/ሚካኤል ገ/መድህን