Home ዜና የአትሌት ጎይተቶም ገ/ስላሴ ወላጆች ባስመዘገበችው ድል  ደስተኞች ቢሆኑም ባለመገናኘታቸው ደስታቸው የተሟላ እንዳይሆን...

የአትሌት ጎይተቶም ገ/ስላሴ ወላጆች ባስመዘገበችው ድል  ደስተኞች ቢሆኑም ባለመገናኘታቸው ደስታቸው የተሟላ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

894

 

ልጃችን ባስመዘገበችው ድል በጣም ደስተኞች ብንሆንም ከልጃችን ጋር ከተገናኘን ሁለት አመት በማስቆጠራችን ደስታችን የተሟላ እንዳይሆን አድርጎታል ሲሉ የአትሌት ጎይተቶም ገ/ስላሴ ወላጆች ተናገሩ፡

በአሜሪካ እየተካሄደ ባለው 18ኛ የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮን በፋሽስቶችና ወራሪዎች የጀኖሳይድ ወንጀል የተፈፀመባትና የተለያዩ ጥቃቶች ከደረስቧቸው የትግራይ እናቶች ማህፀን የተገኙ አልበገሬ ሴት አትሌቶች ድል እየተጧጧፈ ይገኛል፡፡

18ኛው የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮን የማራቶን አዲስ ክብረወሰን ባለቤት ጎይተቶም ገ/ስላሴ ይህንን ድንቅ ድል እንደወትረው ለቤተሰቦቻ ልታበስር አልቻለችም ምክኒያቱም በአለም መድርክ ስማን በማስጠራት ወርቅ ያጎናፀፈቻት አገር በሚመርዋት ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አመካኝነት ትግራይ በከበባና ክልከላ ላይ መሆና ነው፡፡

በዚህም የአትሌትዋ ወላጆች ልጃቸው ባስመዘገበችው ድል በጣም ደስተኞች ቢሆንም ደስታቸውን ለመጋራት ይቅርና በፋሽስቱ ቡድን ከበባና ክልከላ እንዲሁም መሰረታዊ አገልግሎት ሰጪዎች በመዘጋታቸው ከልጃቸው ከተገናኙ ሁለት አመት ገደማ ሆኖብናል ይላሉ፡፡

ይህ ፊታቸው ላይ የሚታየው የናፍቆትና የደስታ የተደበላለቀ ስሜት የብዙዎቹ የትግራይ ወላጆች  ስሜት ነው፤ ልጆቻቸው ግን የትግራይ ትስዕር!! ወኔ መንፈስ አንግበው ፅናታቸው በተግባር በማሳየት አሁንም እንደቀድመው አያቶቻቸው አገሪቱ የወርቅ ሽልማት እንድትቀናጅ የአንበሳውን ድርሻ እየወሰዱ ነው፡፡