Home ዜና የአገው ህዝብ ከጭቆና ለመውጣት ያለው አማራጭ ከትግራይ ሰራዊት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ...

የአገው ህዝብ ከጭቆና ለመውጣት ያለው አማራጭ ከትግራይ ሰራዊት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ መታገል እንደሆነ የአዴን ሰራዊት አባላት ገለፁ፡፡

584

—-

በማንነቱ ብቻ እየደረሰበት ካለው ጭቆና ለመላቀቅ እዱሉን ራስን በራስ የመወሰን መብቱን ለመጠቀም ስለጠየቀ ብቻ የፋሽስቱ አብይ ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች ሰለባ የሆነው የአገው ህዝብ ያለው አንድና አንድ አማራጭ መታገል መሆኑን አምኖ ልክ እንደ ድሮው ከትግራይ ሰራዊት ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ እንደሚገኙ የአዴን ሰራዊት አባላት ገለፁ፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ባኖረው ከበባና ክልከላ ምክንያት በማንነቱ ብቻ ተለይቶ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዲደርሱበትና እንዲያልቅ እየተደረገ ካለው አንዱ የአገው ህዝብ ነው፡፡ ታድያ በማንነቱ ብቻ እየደረሰበት ካለው ጭቆና ለመላቀቅ እዱሉን ራስን በራስ የመወሰን መብቱን ለመጠቀም ስለጠየቀና አልገዛም በማለቱ ብቻ የፋሽስቱ አብይ ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች ሰለባ የሆነው የአገው ህዝብ ያለው አንድና አንድ አማራጭ መታገል መሆኑን አምኖ ልክ እንደ ድሮው ከትግራይ ሰራዊት ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ እንደሚገኙ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰራዊት አባላት ይገልፃሉ፡፡

የአገው ህዝብ ምንም እንኳን በከበባና ክልከላ ውስጥ ቢሆንም ያለችውን በማካፈል በደጀንነት   የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰራዊት ጎን እንዳለ አባላቱ ተናግረዋል፡፡  

አሁንም የትግራይና የአገው ህዝብ ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች በሚያናፍሰው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሳይደናበር ባለው አቅም ደጀንነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ታደሰ ልጃለም