የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መጥቶ ዛሬ ላይ 56 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የፋሽስቱ ቡድን የገንዘብ ሚኒስቴርን ጠቀሰው የሚድያ ተቋማቱ ዘግበዋል፡፡
BBC እና ኳርቲዝ አፍሪካ ድረ ገጽ የዓለም ባንክና የምጣኔ ሃብት ባለሙዎችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ የአምባገነኑ የደርግ ስርዓት ከስልጣን ሲወርድ የሃገሪቷዋ እዳ 9 ቢሊዮን ደላር እንደነበር እና በ2006 የፈረንጀቹ ዓመት ዕዳው ወርዶ 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ይላል የዓለም ባንክ መረጃ የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱ እና በፈረንጆቹ 2020 ላይ ዕዳው 30 ነጥብ 36 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ያስታወሱት ዘገባዎቹ፣ ከሁለት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56 ነጥብ 56 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ጋር ሲነጻጸርም ግማሽ ያህል መሆኑን ያመለከቱት ዘገባዎቹ ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት ቻይናና ፈረንሳይ መሆናቸውን ታወቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ተንታኝ ዶ/ር አየለ ገላን፤ የፋሽስቱ ቡድን ብድሩን ተጠቅሞ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት አለመቻሉ፤ በቂ ሥራ አለመፈጠሩና ገንዘቡ የውጭ ምንዛሬ አለማምጣቱ እዳው እንዲቆለል አድርጎታል ብለዋል፡፡
ፋሽስት አብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የመደበው ከፍተኛ በጀት አሁን በአገሪቱ ከፍትኛ የዋጋ ንረትና የበጀት ቀውስ ማስከተሉን የዘገበው ደግሞ ኳርቲዝ አፍሪካ የተባለ ድረ ገፅ ነው፡፡
ፋሽስት የአብይ ቡድን እና ሸሪኮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ለማድረግ ከአገር ውስጥ አበዳሪ ተቋማት ብድር በመውሰድና ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተመደበው በጀት ወደ ጦርነቱ በማዞር ለወታዳረዊ አገልግሎት ከፍተኛ ወጪ በማስወጣቱ አሁን በሃገሪቷዋ ውስጥ ያጋጠመው ሰፊ የበጀት ቀውስ ምክንያት ሆኗል ብሏል ድረ ገጹ፡፡
ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀው የጀኖሳይድ ጦርነትን ተከትሎ አለም አቀፍ አበዳሪዎችና የልማት አጋሮች ለኢትዮጵያ ይሰጡት የነበረው ብድርና ድጋፍ እንዲዘገይ በማድረጋቸው የአገሪቱ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መንኮታኮቱና ለበጀት አመት ከተመደበው በጀት ውስጥ 25 በመቶ ከውጭ ድጋፍና ከታክስ ይገኛል ተብሎ ከታቀደው እስከ አሁን ድረስም ምንም አለመገኘቱ ተቋማቱ አመልክተዋል፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ እያካሄደ ላለው ጦርነት አገልግሎት የሚውል ከፍተኛ የብር ኖት በማሳተሙ ድጋሜ ከፍተኛ የአገር ውስጥ እዳ እንዲሸከም አድርጎታል ያለው ኳርቲዝ ድረ ገጽ፤ ፋሽስቱ ቡድን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 66 ቢሊዮን የብር ኖቶች ማሳተሙን የፋሽስቱ ቡድን የገንዘብ ሚኒስቴርና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን መረጃ ጠቅሶ ኳርቲዝ ዘግቧል፡፡
ፋሽስት የአብይ ቡድንና ሸሪኮቹ የትግራይን ህዝብ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ለወታደራዊ አገልግሎት ያዋለው ከፍትኛ በጀት አሁን በአገሪቱ ከፍተኛ የዋጋ ንረትና የበጀት ቀውስ ማስከተሉንም ገልጿል፡፡
አገሪቱ አሁን በአንድ ጊዜ ሁለት ጉዳዮችን አንድ ላይ ተጣምረው በምጣታቸው ውጥረት እንድትገባ እድረጓታል ያለው ድረ ገጹ፤ በአንድ በኩል ብሄራዊ ባንክ ለግል ሴክተሮች አነስተኛ የብድር በጀት እንዲመደብና በሌላው በኩል ደግሞ መደበኛ ላልሆኑ የፋይናንስ ገበያዎች ከፍተኛ የሆነ የብድር ፍላጎት መጨመር የዋጋ ንረቱ ይበልጥ እንዲቀጣጠል ማድረጉን አመልክቷል፡፡
በአማረ ኢታይ