—-
በትግራይ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከ170 ሺ በላይ ወገኖች በመቐለ ከተማ ክትባት ማግኘታቸው የትግራይ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ሽሪኮቹ ባደረሱት ከፍተኛ ግፍና መከራ ብሎም የጤና ተቋማት ውድመት ህዝቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ ምክንያት ሆናል፤ በተለይም የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ጣብያዎችና የቫይረሱ የመከላከያ እቃዎች በመዝረፍና በማውደም ብሎም የትግራይ ህዝብ ላይ ባኖሩት ከበባና ክልከላ ምክንያት በቂ የኮረና ቫይርስ መከላከያ ማግኘት አልተቻለም፡፡
ሆኖም የትግራይ ህዝብ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቃ የሚያስችል ክትባት በአለም ጤና ድርጅትና ዩኒሴፍ በተገኘ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ከሃምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በመቐለ ከተማ እየተሰጠ መቆየቱ ይታወሳል የክተባቱ ዘመቻም በመቐለ ከተማ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ የትግራይ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ርእየ ኢሳያስ ተናግረዋል፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ ግን የፋሽስቱ ቡድን የጀኖሳይድ ወንጀሉ አጠናክሮ በመቀጠሉ ቀሪውን የትግራይ የተለያዩ አከባቢዎች ለማዳረስ አልተቻለም፤ ነዳጅ በሰአቱ ባለመግባቱና የህክምና መሳሪያዎች ባለመኖራቸውም ህዝቡ የመጣውን እድል በተያዘው እቅድ እንዳይጠቀም አድርጎታል ሲሉ ዶ/ር ንርእ ይናገራሉ፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በመንታ ምላሱ የአለም ማህብረ-ሰብ እያደናገረ ሰላም ፈላጊነቱን በመግለጫ ጋጋታ ቢያስተጋባም የትግራይ ህዝብ ግን አሁንም በሰው ሰራሽ ረሃብ፤ በመድሃኒትና የህክምና እጦት እንዲሰቃይና እንዲያልቅ ከበባውንና ክልከላውን አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በፍርቱና ገብሩ