Home ዜና የዓለም ምግብና ሕርሻ ድርጅት FAO ከሃምሳ ሺህ ኩንታል በላይ  ማዳበርያ ወደ ትግራይ...

የዓለም ምግብና ሕርሻ ድርጅት FAO ከሃምሳ ሺህ ኩንታል በላይ  ማዳበርያ ወደ ትግራይ ክልል እያጓጓዘ መሆኑን ገለፀ።

529

የዓለም ምግብና ሕርሻ ድርጅት /ፋኦ/ የትግራይ አርሲ አደሮች በምርጥ ዘርና ማዳበርያ እጥረት ምክንያት የዘንድሮ ክረምት እንዳይለፈባቸው እንዲሁም በግዜው ካላገኙ ወቅቱ ሊባክን እንደሚችል በዚህም በጀኖሳይዱ ጦርነት የተጎዳች ትግራይ ያለው የምግብ ቀውስ እንዳይባባስ ከአሁን በፊት ስጋቱን መግለፁን ይታወሳል።

BBC የድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት ሓላፊዋ ጠቅሶ እንደዘገበው እስካሁን 5 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበርያ እንደሚርስና ሌላ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሜትሪክ ቶን ደግሞ በመጓጓዝ ላይ ይገኛል።

FAO ከ USAID እና የስዊዝና ፍሬንች የልማትና ተራድኦ ትብብር ድርጅት በመተባበር በቅርብ ግዜ 12 ሺህ ሜትሪክ ቶን ተጨማሪ ማዳበሪያ በግዢ እንደሚገኝም ቢቢሲ በዘገባው አመላክተዋል።

ግብርና ግብአቶቹ ወደ ትግራይ ለማድረስ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የክረምት ወቅቱ እያለፈ መሆኑ ላነሳነው ጥያቂ ምላሽ አላገኘንም የሚለው የ BBC ዘገባ።

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በጣለው የመንገድና የአገልግሎት ሰጪዎች ክልከላ ምክንያት የትግራይ አርሶ አደሮች ሁኔታ ከአንደበታቸው ለመስማት አልቻልኩም ብሏል።

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና የትግራይ መንግስት የግጭት ማቆም የተናጠል ውሳኔ ካደረጉ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ የተሻለ መጠን ያለው እርዳታ መግባት ጀምሮ እንደነበር የዓለም ምግብ ድርጅት በሪፖርቱ አስታውቀዋል።ያለው BBC

በትግራይ አገልግሎት በተቋረጡ መሰረታዊ ተቋማት ምክንያት የረሃብ ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱም አስታውሰዋል።   

ወራሪዎች በትግራይ በለኮሱት የጀኖሳይድ ጦርነት ተከትሎ ባለፈው ዓመት የትግራይ አርሶ አደሮች ወደ ግብርናቸው በተገቢው ሳይሰማሩ ከባድ ጫና እንደሆነባቸው እና በጦርነቱ ምክንያትም በርካታ አርሶ አሰሮች ከግብርና እንቅስቃሴያቸው በፋሽስቱ ቡድን እና አምባገነኑ የኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች ሊያቋርጡ ተገደው እንደነበር ከሚታረስ የትግራይ መሬት አንድ ሶስተኛ ጥቅም ላይ አለመዋሉን በጥናት በሳትላይት የተደገፈው መረጃ ከአሁን በፊት መዘገቡን አስታውሷል።

በተለይ በወራሪዎች የተያዘ ሰፊ የእርሻ መሬት የሚገኝበት ምዕራብ ትግራይ አብዛኛው ነዋሪ ከአካባቢው የአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ወደሌላ የትግራይ አካባቢዎች የተፈናቀለ ሲሆን ከ60 ሺህ በላይ ደግሞ ድንበርን ተሻግሮ ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል።