Home ዜና የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመበት ካለው የትግራይ ህዝብ ማህፀን የወጡ አትሌቶች መከራ ተቋቁመው ያስመዘገቡት...

የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመበት ካለው የትግራይ ህዝብ ማህፀን የወጡ አትሌቶች መከራ ተቋቁመው ያስመዘገቡት ድል ደማቅ ታሪክ ነው ተባለ፡፡

1009

  

በአሜሪካ ኦርጊዮን ሲካሄድ በነበረው 18ኛው የአለም ኣትሌቲክስ ሻምፒዮን አትሌት ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ ሌሎች ተጋሩ አትሌቶች ባስመዘገቡት ድሎች በአለም አቀፍ መድረክ ስማቸው ደምቆ ይገኛል፡፡

ይሁንና እነዚህ አትሌቶች በግልፅ በአደባባይ ወጥተው የህዝባቸውን ስቃይ ለአለም እንዳያሳውቁ ቢከለከሉም በዚህ አለም አቀፍ መድረክ ተጠናክሮ የቀጠው የትግራይ ተወላጆች ዳያስፖራ ትግል ግን ደምቆ የታየበትና የአለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ቀልብ የሳበ ሆኗል፡

ትግራይና የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች በተለይም በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ላለፉት አመታት አመርቂ ድሎችን በማስመዝገብ የውድድር ድምቀት ሆነው አይረሴ ታሪክ እያስመዘገቡ መጥተዋል፡፡

ታድያ የሀገር ባለውለታ የሆነው የትግራይ ህዝብ ለውለታው ምላሽ የባእድ ሰራዊት ሳይቀር ሰብስበው በላዩ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል በመፈፀም በከበባና ክልከላ ውስጥ አስገብተው ህልውናውን ለማጥፋት ቢሞክሩም የድላቸው መነሻ የሆነችው ትግራይ ግን አሁንም በትግራይ ተወላጅ አትሌቶች አማካኝነት ድሎችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ መካከልም ትግራወይቲ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በአሜሪካ ኦርጊዮን በተካሄደው 18ኛው የአለም ኣትሌቲክስ ሻምፒዮን በሴቶች አምስት ሺህ ሜትር በ14 ደቂቃ 46 ሰከንድና 29 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሯን በአንደኝነት ጨርሳለች፡፡

ይሁንና እነዚህ አትሌቶች በግልፅ በአደባባይ ወጥተው የህዝባቸውን ስቃይ ለአለም እንዳያሳውቁ ቢከለከሉም በዚህ አለም አቀፍ መድረክ ተጠናክሮ የቀጠው የትግራይ ተወላጆች ዳያስፖራ ትግል ግን ደምቆ የታየበትና የአለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ቀልብ የሳበ ሆኗል፡፡

ማአርግ የተባለ ትግራዋይ ዲያስፖራ በዚህ አለማቀፍ መድረክ በትግራይ ተወላጅ ኣትሌቶች የተመዘገበው ድል ለማሳወቅና የትግራይ ህዝብ ድምፅ ለማሰማት የትግራይ ባንዲራ እያውለበለበ ለጀግኖቹ አትሌቶች ድጋፉን የሰጠበት አጋጣሚ ታይቷል፡፡

ማአርግ ለአለም አቀፍ ሚድያዎች በሰጠው ቃለመጠይቅ እነዚህ ጀግኖች አትሌቶች በከበባና ክልከላ ውስጥ ሆኖ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመበት ካለው የትግራይ ህዝብ ማህፀን የወጡና በህዝባቸው እየደረሰ ያለውን መከራ ተቋቁመው ያስመዘገቡት ድል የትግራይ ህዝብ የስነልቦና የበላይነት ያሳያል ብሏል፡፡ 

18ኛው የአለም ኣትሌቲክስ ሻምፒዮን አትሌት ለተሰንበት ግደይ በአስር ሺህ ሜትር ፡ ጎይተቶም ገብረስላሴ በማራቶን አሁን ደግሞ ጉዳፍ ፀጋይ በአምስት ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ለዚህም የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ጀግኖቹ የትግራይ ተወላጆች አትሌቶች ላስመዘገቡት ድል የአምበሳውን ድረሻ መውሰድ ያለበት የጨካኑ ፋሽስቱ ቡድን ባለስልጣናት ሳይሆኑ ፋሽስቱ ባኖረው ከበባና ክልከላ ውስጥ የሚገኙት ቤተሰቦቻቸው ናቸው ይህም በታሪክ መዝገብ ላይ የሚፃፍ ነው ብለዋል፡፡