Home ዜና የፀጥታው ምክርቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰብአዊ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር  እንደሚመክር ተገለፀ፡፡

የፀጥታው ምክርቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰብአዊ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር  እንደሚመክር ተገለፀ፡፡

1096

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ባለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እያጋጠሙ ባሉት እንቅፋቶች ዙሪያ ዛሬ እንደሚመክር Addis Standard ዘግቧል፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች በሚመክረው ስበሰባው የምክር ቤት አባል የሆኑት የአፍሪካ አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው የሚካሄደው፡፡

የወቅቱ የፀጥታው ምክርቤት አባላት ከሆኑት የአፍሪካ አገራት መካከል ጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታና ወደ ትግራይ የሰብአዊ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የፀጥታው ምክር ቤት በስብሰባ እንዲመክርበት ባለፈው ህዳር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፀጥታው ምክርቤቱ በትግራይ ጉዳይ ላይ ባለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እያጋጠሙ ባሉት እንቅፋቶች ዙሪያ እንደሚመክር ተገለፀ፡፡

በስብሰባው ላይ በፀጥታው ምክር ቤት የሰብአዊ መብቶች ዳይሬክተር ጉዳዮች ማርቲን ግሪፍ ማብራሪያ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

ባለፈው ህዳር ወር ሰላምና ደህንነት በአፍሪካ ጉዳይ በሚል ዙሪያ የፀጥታው ምክር ቤት ውይይት አካሂዶ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው 

በኢትዮጵያ የፀጥታ ጉዳይ የፀጥታው ምክር ቤት ከአንድ አመት በፊት በተለያዩ ጉዳዮች በሚመክረው ውይይት እንዲያደርግበት ጥያቄውን ባቀረቡት የአውሮፓና የአፍሪካ አገራት ጥያቄአቸውን በማንሳታቸው እስካሁን ስብሰባው ሳይካሄድ ቆይቷል ብሏል ድረገፁ፡፡

የአገሪቱ መንግስት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥርና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመረ የስብሰባው ተሳታፊዎች ትኩረት እንደሚሰጡበት አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

በተለይም የባንክ፣ የስልክና የመብራት አገልግሎት በትግራይ እንዲጀመር የምክርቤቱ አባላት በአፅንኦት የሚመለከቱት ይሆናል ብሏል ዘገባ፡፡

በተለይም የፌዴራል መንግስቱ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሲባል ግጭትን በጊዜያዊነት ለማቆም መወሰኑን ተከትሎ ወደ ትግራይ እንዲገቡ የተደረጉት የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች 20 ብቻ መሆናቸውን ይህም ከበቂ በታች በመሆኑ የፀጥታው ምክርቤት አባላት ጉዳዩን በትኩረት የሚመለከቱት እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል፡፡

አንዳንድ የምክርቤቱ አባላትም በአገሪቱ ያለው የሰብአዊ መብት ጉዳዮች በተለይም የሰብአዊ መብት ተሟጋች /ሂዩማን ራይት ዎች እና አሚኒስት ኢንተርናሽናል በጋራ ባወጡት ሪፖርትም በውይይት እንዲያነሱት የሚጠበቅ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ላይ ባካሄደው ጦርነት የተፈፀመውን ጆኖሳይድ የሚያጣራ ኮሚሽን ማቋቋሙን ተከትሎ ኮሚሽኑ እንዳይቋቋም ከተቋቋመም አገሪቷ ትብብር የማታደርግ መሆንዋን የገለፀች ሲሆን ለኮሚሽኑ የሚሆን በጀት በአባል አገራት እንዳይመደብ መቃወምዋን ዘገባው አውስቷል፡፡

ተካ ጉግሳ