Home ዜና የፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ጭፍጨፋ፣ በጅምላ ሲረሽኑ ተንቀሳቃሽ ምስል መለጠፉን ብዙዎችን አስደንግጠዋል፡፡

የፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ጭፍጨፋ፣ በጅምላ ሲረሽኑ ተንቀሳቃሽ ምስል መለጠፉን ብዙዎችን አስደንግጠዋል፡፡

2245

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን በጭነት መኪና ተሳፍረው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ በርካታ ሰላማውያን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ሲረሽኑ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማሕበራዊ ሚድያ መሰራጨቱን ተከትሎ በርካቶችን አስደንግጧል፡፡

ሰላማውያን ሰዎችን ከተሳፈሩበት መኪና እያወረዱ ጭካኔ በተሞላበት በጥይት ሲረፈርፏቸው የሚያሳየው ምስል ላይ ሚኒሊክ የሚል ፅሁፍ ያለው ጨርቅ በጭንቅላታቸው የጠመጠሙ ፅንፈኞችቹ የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው፡፡

ፅንፈኞቹ  የፋኖ ታጣቂዎች ይህን አሰቃቂ ግፍ ሲፈፅሙ በስቃይ ላይ የነበሩ ተጎጂዎች ጥይት አታባክኑ ተሰቃይተው ይሙቱ ሲሉ በንግግራቸው ይደመጣሉ፡፡ ቀጥሎ የሚቀርበው ተንቀሳቃሽ ምስል እድሚያቸው ከ 16 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ፣ ነብሰ ጡሮች እና ተደራራቢ በሽታ ያለባቸው ሰዎች እንዳያዩት እናስጠነቅቃለን፡፡

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን የጭካኔ ጥግ የተላበሰ የጦር ወንጀኛ እና ዘራፊ ቡድን መሆኑን ፋሽስቱ አብይ አሕመድ ሰሙኑ በፓርላማ ቀርቦ ማመኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገርም አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሂይማን ራይትስ ዎች እና አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል ከወር በፊት ባወጡት የጋራ የጥናት ሪፖርት ተስፋፊው አማራ ሀይል ይሄው ፅንፈኛ የፋኖ ቡድን በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሰላማውያን ወገኖችን በጅምላ በመግደል፣ ፆታዊ ጥቃት በመፈፀም ፣ እንዲሁም የዘር ማፅዳት ወንጀል የፈፀሙ የጦር ወንጀለኞች  መሆናቸውንም ተቋማቱ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡