Home ዜና የፋሽስቱ አብይ ቡድን እና የአወል አርባ ሴራ ልንመክተው ይገባል ሲሉ የትግራይና የዓፋር...

የፋሽስቱ አብይ ቡድን እና የአወል አርባ ሴራ ልንመክተው ይገባል ሲሉ የትግራይና የዓፋር ሃገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

1165

—–

የትግራይና የአፋር ህዝብ ደመኛ ጠላት የሆኑት የፋሽስቱ አብይ አሕመድና የአወል አርባ ሴራ ተረድተን እንደቀድሞው አንድነታችንን በማጠናከር ከፌደራሊስት ሀይሎች ጎን በመሆን ጠላቶቻችንን ልንመክታቸው ይገባል ሲሉ የሁለቱ የአገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

ይህ የተገለፀው የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የትግራይና የአፋር ፌደራሊስት ሀይል አመራሮች የተገኙበት የትግራይና የአፋር ህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር በተካሄደው መድረክ ነው፡፡

የትግራይና የአፋር ህዝቦች ከጥንት ጀምሮ በብዙ መልኩ የተጋመዱ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው፤ ታድያ ለስልጣኑ ሲል ምንም ከማድረግ ወደኋላ የማይለው የፋሽስቱ ቡድን ተባባሪ አወል አርባ ግን በሁለቱም ህዝቦች መሀል ቅራኔ ለመፍጠር ታሪክ ይቅር የማይለው ድርጊት እየፈፀመ እንዳለ የትግራይና የአፋር የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡

የሀገር ሽማግሌዎቹ በጠላት ሴራ ሳንደናገጥ የቀደመው ሰላማችንና አንድነታችን ለመመለስ በአብሮነት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የራያ ዓዘቦ ወረዳ አስተዳዳሪ ታጋይ ሓየሎም ረዳኢ የጠላት ሴራ ተረድተን እንደቀድሞው አንድነታችንን በማጠናከር ከፌደራሊስት ሀይሎች ጎን ሆነን ጠላቶቻችንን ልንመክታቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ታጋይ ሓየሎም ረዳኢ የራያ ዓዘቦ ወረዳ አስተዳዳሪ

የአፋር ፌደራሊስት ሀይል ምክትል ፕሬዝደንት ታጋይ ሓጂ ያሲን መሓመድ በበኩላቸዉ በፋሽስቱ አብይ አሕመድና በአወል አርባ ተግባር ሳንደናበር ከፌደራሊስት ሀይል ጎን ሆነን የሁለቱም ህዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ታጋይ ሓጂ ያሲን መሓመድ የአፋር ፌደራሊስት ሀይል ምክትል ፕሬዝደንት

በዊንታ ዘላለም