Home ዜና የፋሽስታውያን ሴራ ያጋለጠ ሪፖርት

የፋሽስታውያን ሴራ ያጋለጠ ሪፖርት

984

Human_Rights_Watch እና Amnesty_International ይፋ ያደረጉት የጥናት ሪፖርት የፋሽስቱ ቡድንና ተስፋፊ የአማራ ሊሂቃን በምዕራብ ትግራይ የፈፀሙትን የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል ለማድበስበስ የሸረቡት ሴራ ያጋለጠ ነው ሲሉ የህግ ምሁራን ገለፁ፡፡

በተያያዘ ዜና Human_Rights_Watch እና Amnesty_International ሪፖርት ላይ በምዕራብ ትግራይ የሚገኙ ሃይሎች ትጥቃቸው እንዲፈቱ የቀረበው ምክረ ሐሳብ በተመለከተ ቀዳሚውና ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ መምጣት ያለበት ትጥቅ መፍታት ብቻ ሳይሆን ወራሪ ሐይሎች ከያዙት የትግራይ መሬት ለቀው መውጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ የህግ ምሁራን ገልፀዋል፡፡

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች የሆኑት Human_Rights_Watch እና Amnesty_International በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል በተመለከተ ለ15 ወራት ባደረጉት ጥናት መሰረት ከ240 በላይ ገፆችን የያዘ የጋራ ሪፖርት ሰሞኑን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ጉዳይ አስመልክተን ያነጋገርናቸው የህግ ባለሙያዎቸ ተቋማቱ ይፋ ያደረጉት የጥናት ሪፖርት በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ወደር አልባ ግፍና ጭፍጨፋ ያጋለጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Human_Rights_Watch እና #Amnesty_International ያወጡት የጥናት ሪፖርት በምዕራብ ትግራይ ከተፈፀመው የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል ባለፈ የጀኖሳይድ ወንጀል መፈፀሙንም ሪፖርቱ አመላክትዋል በማለት የፋሽስቱ በድንና የተስፋፊው አማራ ሊሂቃን የፈፀሙት ተግባር ለማድበስበስ የሸረቡትን ሴራ ያለጠ ሪፖርት ነው ሲሉም የህግ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

የጥናት ሪፖርቱ መልካም ጅምር መሆኑን የሚገልፁት የህግ ባለሙያዎቹ በተለይም በሴራዎች ለማድበስበስ ሲሞከር የነበረውን የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ጭፍጨፋና ግፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሄዱበት እንቅስቃሴ የሚበረታታና ኣድናቆት የሚቸረው ጥናት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

በሪፖርቱ በርካታ ዝርዝር ነገሮች ተጠቅሰዋል ያሉት የህግ ባለሙያዎቹ ቢሆንም ግን የተፈፀመው ወንጀል ከእቅዱ እስከ አፈፃፀሙ በበላይነት ሲመሩ የነበሩት ፋሽሰቱ የአብይ ቡድን፣ የአምባገነኑ የኢሳያስ መንግስትና  የተስፋፊው የአማራ  ሃይሎች በግልፅ ቋንቋ የወንጀሉ ፈፃሚዎች መሆናቸውን በሪፖርቱ መመላከት ነበረበት ሲሉም ሐሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱም የሰብዓዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ያወጡት ሪፖርት ሌሎች በትግራይ ጉዳይ ጥናት ለሚያደርጉ አለምአቀፍ ተቋማት መነሻ የሚሆንና የተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት በአግባቡ እንዲገነዘቡ ያደረገ ጥናት ነው፣ ስለሆነም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ይህንን በመመልከት በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የተፈፀሙ ወንጀሎች በማጣራት ወደ ተግባራዊ እርምጃ መግባት አለበት ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቹ Human_Rights_Watch እና Amnesty_International በጋራ ባወጡት ሪፖርት ላይ በምዕራብ ትግራይ የሚገኙ የተስፋፊው የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና የፋኖ ቡድን ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተጠይቋል፡፡ ይሁን እንጂ ያነጋገርናቸው የህግ ሙሁራን እንደሚገልፁት ትጥቅ ማውረድ ብቻ ሳይሆን ቀዳሚውና ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ መምጣት ያለበት እነዚህ ወራሪ ሃይሎች ከያዙት የትግራይ መሬት ለቀው መውጣት ይኖርባቸዋል መሆን ነበረበት፡፡

ተቋማቱ በሪፖርታቸው የምዕራብ ትግራይ ብለው ያካተቱት አካባቢ በታሪክ እንዲሁም በሃገሪቱ ህገመንግስት መሰረት የትግራይ ሉኣላዊ ግዛት መሆኑን እየታወቀ እነዚህ ሃይሎች በወረራ በተቆጣጠሩት የትግራይ ግዛት የሚያቆያቸው ምንም ዓይነት ሁኔታ መኖር የለበትም ሲሉም የህግ ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሁዩማን ራይትስዎች በሪፖርታቸው ያካተቱትና ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ የሆነው ወደ ምዕራብ ትግራይ ሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲገባ መጠቆማቸው ተቀባይነት የሌለውና ከዓለምአቀፍ የህግ ስምምነቶች አኳያ የማያሰኬድ መሆኑን የህግ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የጥናት ሪፖርቱን በማስመልከት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የኤርትራን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ተስፋፊው የአማራ ሃይል ደግሞ ከትግራይ ምድር በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡