Home Uncategorized የ2014 ዓ.ም የአሸንዳ በዓል በርካታ ጀግኖች ሴት ታጋዮችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት...

የ2014 ዓ.ም የአሸንዳ በዓል በርካታ ጀግኖች ሴት ታጋዮችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በመቐለ ከተማ ተከበረ፡፡

1845

የትግራይ እናቶች በነሱ ላይ በወረደው ግፍና በደል ሳይንበረከኩ የትግራይን ህዝብ ትግል አፈር ልሶ እንዲነሳ እንዳደረጉና አሁንም ጀግኖች ሴት ታጋዮች የትግራይን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ዘብ ቆመው እንደሚገኙ በበአሉ ተገልጿል፡፡

ትግራይ ቴሌቪዥን ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር የ2014 ዓ.ም አሸንዳ በዓል በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ከሚገኙ ጀግኖች ሴት ታጋዮች ጋር አክብሮታል፤ የዚህ ተቀጥያ በመቐለ ከተማም የአሸንዳ በዓል የተከበረ ሲሆን በዝግጅቱ የተገኙት ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ የትግራይ እናቶች በነሱ ላይ በወረደው ግፍና በደል ሳይንበረከኩ የትግራይ ህዝብ ትግል አፈር ልሶ እንዲነሳ አድርገዋል ይላሉ፡፡

የትግራይ ህዝብ የሰላምን ዋጋ ከማንም በላይ ጠንቅቆ የሚያውቅ እንደሆነ የገለፁት ጀነራል ዘውዱ እነዚህ ጀግኖች ሴት ታጋዮችም የትግራይን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ዘብ ቆመው አሸንዳን እያከበሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ጀግኖች ሴት ታጋዮች በበኩላቸው ቀጣይ አመት ትግራይ ነፃና ሰላምዋ የተጠበቀላት በማድረግ የአሸንዳ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እንደሚጥሩ ገልፀዋል፡፡

በዓሉ በርካታ ጀግኖች ሴት ታጋዮችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

ዊንታ ዘላለም