Home ዜና ዶ/ር ደብረፅየን አምባገነኑ ኢሳያስ በተለመደው ባህሪው የአለምን ማህበረ-ሰብ ለማደናገርና ለማታለል  እየሰራ መሆኑን...

ዶ/ር ደብረፅየን አምባገነኑ ኢሳያስ በተለመደው ባህሪው የአለምን ማህበረ-ሰብ ለማደናገርና ለማታለል  እየሰራ መሆኑን አጋለጡ፡፡

992

የትግራይ ህዝብ ዘር ለማጥፋት በአለም  ታይቶ የማይታወቅ  ግፎችን የፈፀመው አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ  በወረራ ከያዘው የትግራይ መሬት  ሳይወጣና   አሁንም ግፎችን ከመፈፀም  ሳይቆጠብ በተደጋጋሚ ሊወሩኝ ነው በማለት እያቀረበው ያለው አቤቱታ  የአለምን ማህበረ-ሰብ ለማደናገርና ለማታለል መሆኑን  የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኣል  በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በሰጡት ማብራርያ ገለፁ፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ኤርትራን ጨምሮ ማንንም የመውረር  ፍላጎት  እንደሌለው በመግለፅ ሆኖም በህልውናውና በግዛታዊ አንድነቱ  ግን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነውም ብለዋል ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኣል  በመግለጫቸው ፡፡                                                              

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፂዩን ገብረሚካኣል  በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ አምባገነኑ ኢሳያስ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት በተደረገው የጀኖሳይድ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ብቻ  ሳይሆን  የወንጀሉ ዋነኛ ጠንሳሽ መሆኑን በመግለፅ በትግራይ ህዝብ ላይ የቻለውን የግፍ አይነት የፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አምባገነኑ ቂም በቀሉን እንደተወጣና አጠናቅቄኣለሁ ብሎ ያስብ አንደነበር በመጥቀስ  አሁን ላይ ሊወሩኝ እየተዘጋጁ ነው የሚል ጩኸት ማሰማት መጀመሩ የትግራይ ህዝብ አቅምና ጉልበት ያሳየ ነውም ብለዋል  ደ/ር ደብረፂዩን በመግለጫቸው፡፡

ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኣል 

የትግራይ ህዝብና መንግስት ኤርትራንም ጨምሮ ማንንም የመውረር ፍላጎት የለውም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ነገር ግን በህልውናውና ግዛታዊ አንድነቱ ሲል መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነውም ብለዋል፡፡

ሆኖም አምባገነኑ ኢሳያሰ አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እየፈፀመና በወረራ ከያዘው የትግራይ መሬት ሳይወጣ እያሰማው ያለው የይስሙላ ጩሀት ተቀባይነት የለለው ስለሆነ ከትግራይ መሬት መውጣት አለበት ብለዋል፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ለሰላም ያለው ዝግጁነት የአለም ማህበረ-ሰብ ሊያውቅ ይገባል ያሉት ዶ/ር ደብረፂዩን በሰላም የማይፈታ ከሆነ ግን በህዝባችን ላይ በደልና ግፍ እየተፈፀመ መመልክት ሰለማንችል ሌላ አማራጭ ለመጠቀም እንገደዳለንም ብለዋል በመግለጫቸው ፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን በመግለጫቸው አምባገነኑ ኢሳያስ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈለገውን የሚያደርግበት ጊዜ ማብቃቱን በመግለፅ  አሁን ላይ እያሰማ ያለው የድረሱልኝ ጩኸት የትግራይን ህዝብ ፅናትና አቋም ያሳየ ሲሆን በሌላ በኩል  አጭበርባሪነቱን ያሳያልም ብለዋል፡፡

ፍሬሂዎት ተ/መድህን