Home Uncategorized ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ያደረሰዉን ጥቃት በዋሽንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተቃዉሞ...

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ያደረሰዉን ጥቃት በዋሽንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተቃዉሞ ሰልፍ ገለፁ፡፡

1396

በጎንደር ከተማ በሙስሊሙ ማሕበረ-ሰብ ላይ በፅንፈኛው ቡድን የተፈፀመው ጥቃት እና የንብረት ዉድመት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መልኩ የተፈፀመ ድርጊት ነው ሲሉ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የተቃዉሞ ሰልፍ የተገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ገለፁ፡፡

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ያደረሰዉን ጥቃት በመቃወምና ፍትህ ላላገኙት ሙስሊሞች ድምፃቸውን ያሰሙት ሰልፈኞቹ ድርጊቱ እጅጉን እንዳሳዘናቸዉ በመግለፅ ለተጎዱት ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ፋኖ በተባለው ፅንፈኛ ታጣቂ ቡድን በሙስሊም ማሕበረ-ሰብ ላይ የተፈፀመው ግድያና የንብረት ውድመት በመቃወም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተቃዉሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ያደረሰዉን ጥቃት በመቃወምና ፍትህ ላላገኙት ሙስሊሞች ድምፅ ለመሆን ትውልደ ኢትዮጵያዉያን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ የኢትዮጽያ ኤምባሲ ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሂደዋል ፡፡

የተቃዉሞ ሰልፉን ያስተባበሩት አቶ መሃመድ ሁሴን መሃመድ በጎንደር ከተማ በሙስሊሙ ማሕበረ-ሰብ ላይ በፅንፈኛው ቡድን የተፈፀመው ጥቃት  እና የንብረት ዉድመት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መልኩ የተፈፀመ ድርጊት ነው ብለውታል፡፡

ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን በጎንደር ሙስሊሞች ላይ በፈፀመው ጥቃት ቤተሰባቸውን ያጡት አቶ ኑረዲን መሃመድ አና የደረሰዉን ግፍ በመቃወም በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት ኣቶ ኣደም ኣለሙ ድርጊቱ እጅጉን እንዳሳዘናቸዉ በመግለፅ ለተጎዱት ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በፍረህይወት ተ/መድህን