ፋሽስቱ አብይ ቡድን የወላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ለማፈን የተለያዩ የብሄሩ ተወላጆች የፖለቲካ አመራሮችና አባላትን ጨምሮ በጅምላ እያሰረ መሆኑን ተገለፀ፡፡የወላይታ ህዝብን ልሳን ለመዝጋት ታልሞ በህዝቡ መሪዎች ላይ የፋሽስቱ ቡድን እየወሰደ ያለዉን የጅምላ እስራት እርምጃ ከምን ግዜዉም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም በፖለቲካ ልዩነት ብቻ ብዙሃንን እያሰረና እያሰቃየ ይገኛል ሲሉ የብሄሩ ተወላጆች ለOMN በስልክ ተናግረዋል፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በወላይታ የተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ እስራት አጠናክሮ መቀጠሉን OMN ዘግቧል፡፡ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆን ጨምሮ ጋዜጠኞች፤ የመብት ተሟጋቾች፤ አርቲስቶች፣ መምህራን፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራርና አባላት እና በርካታ ወጣቶች በፋሽስቱ ቡድን የፀጥታ ሃይሎች ታፍነዉ መወሰዳቸዉን በዘገባው ተመላክቷል፡፡
የወላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዉ እንዲቀለበስ እና የወላይታ ህዝብ ልሳን ለመዝጋት ታልሞ በህዝቡ መሪዎች ላይ የፋሽስቱ ቡድን ያላንዳች ጥፋት እየወሰደ ያለዉን የጅምላ እስራት እርምጃ ከምን ግዜዉም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም በፖለቲካ ልዩነት ብቻ ብዙሃንን እያሰረና እያሰቃየ ይገኛል ሲሉ የብሄሩ ተወላጆች ለOMN በስልክ ተናግረዋል፡፡
የወላይታ ህዝብ ራስን በራስ የመወሰን እና የማስተዳደር የመብት ጥያቄ በወረዳና በዞን ምክር ቤት ሰፊ ዉይይት ተደርጎበት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በሙሉ ድምፅ ወደ ደቡብ ክልል ምክር ቤት መላኩን ያወሳዉ ዘገባዉ የክልሉ ምክር ቤት ላለፉት አራት አመታት ጥያቄዉን አፍኖ መቆየቱንም ተገልጿል፡፡ከወላይታ አስተያየታቸዉን ለ OMN በስልክ ከሰጡ የብሄሩ ተወላጆች መካከል አንደኛዉን አስተያየት ሰጪ ከደቂቃዎች በኋላ በፋሽስቱ ቡድን የፀጥታ ሃይሎች ታፍኖ መወሰዱን OMN ዘግቧል፡፡
በሙሉብርሃን ዳርጌ