Home ዜና ፋሽስት የአብይ ቡድን እያካሄደ ያለውን የጋዜጠኞች አፈናና ወከባ በአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት እያሽቆለቀለ...

ፋሽስት የአብይ ቡድን እያካሄደ ያለውን የጋዜጠኞች አፈናና ወከባ በአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት እያሽቆለቀለ መምጣቱ አልጀዚራ ዘገበ፡፡

1275

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆናቸው  በዘገባው ያመላከተው Al-jazeera እስከ አሁን 22 የሚድያ ባለሙያዎች በገፍ ታፍነዋል ብሏል በዘገባው፡፡

Al-jazeera ለደህንነቱ ሲል ስሙን መግለፅ ያልፈለገን ጋዜጠኛ በመጥቀስ እንደዘገበው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በሚድያ ሰዎች በተለይም የእስር ትኩረቱ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃ የሚያሰራጩ የይዘት አምራቾች በሆኑ ጋዜጠኞች ላይ ነው፡፡

በተጨማሪ ጋዜጠኛው ፋሽስት የአብይ ቡድን  አሁን ምን ያህል ጋዜጠኞች ሊያስር እንደሚችል ነው መጠየቅ የምፈልገው ብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ በዚህ ወር ውስጥ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 19 የሚድያ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ከዚህ ቀደም the economist   ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነር የስራ ፈቃዱ ተነጥቆ ከአገር እንደተባረረ ያስታወሰው የ Al-jazeera ዘገባ በአሁኑ ወቅት ለእስር የተዳረጉ የሚድያ ባለሙያዎች ቁጥር ወደ 22 ከፍ ማለቱን ያስረዳል፡፡

ወከባውና አፈናው የበረታው በፋሽስት የአብይ ቡድን ቅጥረኛ ወታደሮችና የወንጀለኞች ስብስብ በሆነውን ፋኖ መካከል ውግያ መቀስቀሱን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

አብዛኞቹ ለእስር የታደረጉት የሚድያ ባለሞያዎች ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጎን በመሰለፍ በትግራይ ህዝብ በታወጀው ጀኖሳይድ ጦርነት ሰፊ የሚድያ ቅስቀሳ እና በትግራይ ህዝብ የጥላቻ ዘመቻ በማድረግ ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸው ይታወቃል።