Home ዜና UN አጣሪ ኮሚሽን በትግራይና ኦሮሚያ አሁንም ግፎች ተጠናክረው መቀጠላቸው እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

UN አጣሪ ኮሚሽን በትግራይና ኦሮሚያ አሁንም ግፎች ተጠናክረው መቀጠላቸው እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

645

——

የተ.መ.ድ አጣሪ ኮሚሽን በትግራይና ኦሮሚያ አሁንም ግፎች ተጠናክረው መቀጠላቸው እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ያለፉት ወራት የስራ ክንውን ትናንት ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት የቃል ሪፖርት በቀረበበት ወቅት የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ኬንያዊቷ ቤቲ ሙራንጊ ኮሚሽኑ ግፎችን ለመመርመር ያልተገደበ እንቅስቃሴ ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

አጣሪ ኮሚሽኑ ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት 50ኛ ሰብሰባ ኮሚሽኑ ከተቋቀመበት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ ያከናወናቸው ስራዎች አስመልክቶ በኮሚሽኑ ሊቀመንበር የቃል ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ኮሚሽነሯ ባቀረቡት ሪፖርት ኮሚሽኑ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የመመርመር ስራውን እንዲጀምር እንዲችል ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ፈቃድ ማግኘቱን ጠቅሰው ሰብአዊ የመብት ረገጣዎች የተፈፀሙባቸው አካባቢዎችን መለየት  ከግፉ የተረፉት፣ ሰለባዎችና የአይን እማኞችን ለማነጋገር እንደሚችሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

AFP እንደዘገበው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በመርማሪ ኮሚሽኑ መቋቋም ከመጀመሪያውኑ በመቃወም ለኮሚሽኑ ስራ እንደማይተባበር ሲያስታውቀ የቆየ ቢሆንም አሁን አቋሙን በመቀየር ከኮሚሽኑ ጋር መነጋገር ጀምሯል፡፡

ኮሚሽኑ በሐምሌ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡