—-
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ሃመር የትግራይ ጦርነት በሰለማዊ ውይይት እንዲፈታ እና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን አሜሪካ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ገለጹ፡፡
የትግራይ መንግስትና የፋሽስቱ ቡድን ከጠበ ጫርነት ንግግር ተቆጥበው ወደ ድርድር እንዲገቡም አሜሪካ ጥሪ አቀርባለች፡፡
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው አምባሳደር ማይክ ሃመር ከአውሮፓ አቻቸው አነቴ ዌበርና እና ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የትግራይ ጦርነት በሰለማዊ ድርድር እንዲፈታ ያለመ ባለፈው ሳምንት መቐለ መምጣታቸውን እና ከትግራይ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡
አምባሳደር ማይክ ሃመር በአዲስ አበባና መቐለ ጉብኝት ካደረጉ በኃላ በነዳጅ እጥረት ምክንያት መቐለ ያለው እህል ወደ እርዳታ ፈላጊ አለመጓጓዙን መገንዘባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
በቆይታቸው ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት የተቋቋመው አጣሪ ኮምሽኑ ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ አከባቢዎች በነጻ ገለልተኛ ሆኖ እንዲያጣራ ሁኔታዎች አንዲመቻቹ ከስምምነት ላይ መደረሱን የገለጹት ማይክ ሃመር ይህም ተግባራዊ እንዲሆን ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
የትግራይ ጦርነት በሰለማዊ ውይይት እንዲፈታ ብሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን አሜሪካ በትኩረት እየሰራች ነው ሲሉም ልዩ መልእክተኛው ማይክ ሃመር ለቢቢሲ የገለፁት፡፡
በተያያዘ ዜና በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫም የትግራይ ጦርነት በሰለማዊ ድርድር እንዲፈታ ሁለቱም ሃይሎች ድርድር እንዲጀምሩ አሜሪካ አንደምታበረታታ አመልክቷል፡፡
ማይክ ሃመር ከትግራይ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፋሽስቱ ቡድን አና ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ጋር በሰለማዊ ድርድር ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ያወሳው ኤምባሲው የሰላም ድርድር እንዲጀመር ማበረታታቸው እና በአጭር ጊዜ እንዲጀምሩ አሜሪከ ትፈልጋለች ሲል ገልጿል፡፡
ማይክ ሃመር በተጨማሪም ከአንድ አመት በላይ በትግራይ የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግለቶች ስራ ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ መምከራችውን የአሜሪካ ኤምባሲ አመላክቷል፡፡
ይህ ውይይትም አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት፣ አሜሪካ እና አውሮፓ የድርድሩ አካል ሆነው ይሳተፋሉ።
ወ/ሚካኤል ገ/መድህን