Home ዜና በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ኣከባቢዎች በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትና በፋሽስቱ የአብይ ቡድን መካከል ጦርነት...

በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ኣከባቢዎች በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትና በፋሽስቱ የአብይ ቡድን መካከል ጦርነት መቀጠሉን Omn ዘገበ።

1990

—- 

በደቡባዊ ፣ማእከላዊ ፣ምዕራባዊ እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ የኦሮምያ ዞኖች ሰሞኑን በአከባቢያቸው በሁለቱም ሃይሎች መካከል ከባድ ጦርነት መካሄዱን omn የኣከባቢው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ 

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በበኩሉ በተለያዩ አከባቢዎች ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሰራዊት ጋር መዋጋቱንና የፋሽስቱ ሃይሎች ከባድ ኪሳራ ማድረሱን መግለፁ omn ጨምሮ ዘግቧልል።

በተጨማሪ በምዕራብ ሸዋ ዞን እልፈታ ሚዳቅኚ፣ ዳዲና ዳኖ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን ጉመየል ዶሎ ወረዳ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጅማ ኣርጆ ወረዳ ፣በቀሌም ወለጋ ዞን ኣንፊሌ ወረዳ እንዲሁም በኣርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ከፋሸስቱ ሃይሎች ጋር ሰሞኑኑ ውግያ ማድረጉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለፁን omn ዘግቧል።

በነዚህ ውግያዎችም በመንግስት ሃይሎች ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱንና በርካታ ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸውን ጠቁሞ    በውጊያው ሁለት ብሬንን ጨምሮ ከ30 በላይ ጠመንጃዎችን እንደማረከም ተገልጿል።