Home ዜና በፋሽስቱ የአብይ ቡዱን የጄኖሳይድ ጦርነት ማብቂያ ሳይበጅለት የአለም ባንክ ለመስጠት ያቀደው የገንዘብ...

በፋሽስቱ የአብይ ቡዱን የጄኖሳይድ ጦርነት ማብቂያ ሳይበጅለት የአለም ባንክ ለመስጠት ያቀደው የገንዘብ ድጋፍ ሊታሰብበት እንደሚገባ  ተጠየቀ፡፡

852

በፋሽስቱ የአብይ ቡዱን የጄኖሳይድ ጦርነት ማብቂያ ሳይበጅለት የአለም ባንክ ለመስጠት ያቀደው የገንዘብ ድጋፍ ሊታሰብበት እንደሚገባ  ተጠየቀ፡፡

—-

ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን በአሁኑ ወቅት በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው የጄኖሳይድ ጦርነት ማብቂያ ሳይበጅለት የአለም ባንክ ለመስጠት ያቀደው የገንዘብ ድጋፍ ከመልቀቁ በፊት ጉዳዩን ሊያጠነው እንደሚገባ አለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማሕበር ጠየቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት በማናቸውም አካላት ለፋሽስቱ ቡድን የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የጄኖሳይድ ጦርነት ከማባባስ አልፎ ሌላ ለውጥ የማያመጣ መሆኑን ማሕበሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ተከትሎ የተከማቸው የሃገሪቱ አንጡራ ሃብት የፋሽስቱ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ ላወጀው የጄኖሳይድ ጦርነት በማዋል አሰቃቂና አውዳሚ የሆኑት ክስተቶች መፈፀሙን አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የጦርነቱ ሁኔታ ጋብ ያለ ቢመስልም ከአንድ አመት በላይ የዘለቀ ክልከላና ከበባ ተጠናክሮ መቀጠሉን  የማሕበሩ መግለጫ አስረድቷል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የትግራይ ህዝብ ምግብ ነዳጅና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዳያገኝ በማድረግ ለከፋ ስቃይና ሰው ሰራሽ ረሃብ መዳረጉን ዓለምአቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር ገልጿል፡፡

በትግራይ የነበሩት መሰረተ ልማቶችና እንደ ህክምናና ትምህርት ቤቶች የመሳሰሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች በፋሽስቱ ቡዱን እንዲወድሙ መደረጉን ያወሳው መግለጫው ይህንኑ ተከትሎም የትግራይ ህዝብ ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ እየተዳረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ህዝብ ላይ ያለው ስቃይና መከራ ተጠናክሮ እየቀጠለ ባለበት ወቅት በአለም ማህበረ-ሰብ የተረሳ እስኪመስል  መድረሱን የማሕበሩ መግለጫ አስረድቷል፡፡

ለአብነትም ክልከላውን ተከትሎ ሰባት ሚልዮን የሚሆን የትግራይ ህዝብ ለከፋ ርሃብና ስቃይ እንዲሁም ከማናቸውም የህክምናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ተከልክሎ መቀጠሉን መግለጫው አመልክቷል፡፡

እንዲሁም የፋሽስቱ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው የጀኖሳይድ ጦርነት ከ500 ሺህ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ለሞት መዳረጋቸውን፣ ከ150 ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞችና ባለሙያዎች ከ19 ወራት በላይ ደመወዛቸው ሊያገኙ አለመቻላቸው ዓለምአቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር መግለጫ አስረድቷል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን ተከትሎ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውንና ለሶስት አስርት አመታት የትግራይ ህዝብ ተራራ ንዶ ያለማው የተፈጥሮ ሃብትም በከፍተኛ ሁኔታ መውደሙን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ከፋሽስቱ ቡድን አመራሮች ንግግሮች መረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት በወታደራዊው ዘርፍ አጋጥሞት ያለው የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ከተለያዩ የውጭ አገራት በሚያገኘው ገንዘብ የወታደራዊ ሃይሉንና የደህንነት ዘርፉን ለማጠናከር እንዳቀዱ መረዳት ይቻላል ያለው የማሕበሩ መግለጫ ይህም ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ሌላ ጦርነትና ውድመት ለማካሄድ ማቀዱን ያመላክታል ብሏል ዓለምአቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር መግለጫ፡፡

በሃገሪቱ ያለው እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ የአለም ባንክ ለማድረግ የወሰነውን የገንዘብ ድጋፍ የፋሽስቱ ቡዱን በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች እንዲጠቀምበት ለማስቻል ነው ማለቱ ግልፅ አይደለም ብሏል ማሕበሩ፡፡

የአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፉ ቢለቅ እንኳን አሁን ባለው ሁኔታ የጆነሳይድ ጦርነት የታወጀበት የትግራይ ህዝብ እንዴት በፋሽስቱ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል ፣ ራሱ ያወደማቸው የመሰረተ ልማቶችና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎቶች መስጫ ተቋማትስ እንዴት ሊገነባቸው ይችላል የሚለው ለማወቅ ክትትል ለማድረግና ገንዘቡ ለታለመለት ዓላማ ስለመዋሉ የሚታወቅበት ሁኔታ እንደሌለ ዓለምአቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር መግለጫ አመልክቷል፡፡

በመሆኑም የድጋፍ ገንዘቡ ከመለቀቁ አስቀድሞ የፋሽስቱ ቡዱን በገዛ ዜጎቹ ላይ እያደረሰ ባለው የጀኖሳይድ ጦርነት ለተጎዳው የትግራይ ህዝብ ሌላ ጉዳት ለማድረስ እንዳይውል የአለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጉዳዩን ሊያጤነው እንደሚገባ ማሕበሩ በመግለጫው ጠይቋል፡፡

ተካ ጉግሳ