Home ዜና የምእራብ ትግራይ ተፈናቃዮች በመድሃኒትና በምግብ እጦት ምክንያት ዜጎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡

የምእራብ ትግራይ ተፈናቃዮች በመድሃኒትና በምግብ እጦት ምክንያት ዜጎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡

1150

ፋሽስቱ አብዪ አህመድና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖሩት ከበባና ክልከላ አንዲት አራስ ጨምሮ ስድስት ሰዎች በመድሃኒትና በምግብ እጦት ምክንያት ለህልፈት ተዳረጉ፡፡

እነዚህ ከምእራብ ትግራይ በወራሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአክሱም ከተማ ተጠለው የሚገኙ ተፈናቃዮች አሁን ላይ ሁሉም ወገኖች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸውን  ተፈናቃዮች ተናግረዋል።

በፋሽስቱ ቡድን በተስፊው የአማራ ሃይል እና በአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ላይ ባካሄዱት የጀኖሳይድ ጦርነት  አሁንም ድረስ ከፍተኛ ግፍ እየደረሰበት ያለው የምእራብ ትግራይ ህዝበ አሁንም በከበባው ምክንያት በከፍተኛ ጉዳት ላይ ይገኛል፡፡

ከምዕራባዊ ዞን #ቃፍታ ሑመራ አደባይ ወረዳ ተፈናቅለው  በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮችም በመጠለያው ለአስራ ሰባት ወራት ያህል በመጠለያ ቢቆዩም ምንም እርዳታ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

በዚህ ሳብያም በመጠለያ ጣብያው የሚገኙ ወገኖች በከፍተኛ ረሀብና በመድሃኒት እጥረት እየተሰቃዩ  እንደሚገኙ የመጠላያ ካምፕ አስተባባሪ አቶ ገብረ ተክላይ ይናገሩሉ፡፡

በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ የተፈናቃዮች ካምፕ የሚገኙት ከአስራ አምስት ሺ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች በአንድ ክፍል ብዛት ያለው ሰው በመሰባሰቡ መክንያት ለተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸው ይገልፃሉ።

በዚህም በመጠለያው የሚገኙ አረጋውያን፣ እናቶች፣ ህፃናትና ወጣት ተፈናቃዮች በተለይ ደግሞ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ያላቸው ሰዎች በከፍተኛ የርሃብ አለንጋ እየተገረፉና በመድሃኒት እጥረት ለከፋ ችግር በመጋለጣቸው ሳብያ አንዲት አራስ ከነ ልጅዋና ሌሎች ስድስት በመጠለያው ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው ተናግረዋል። 

ከተፈናቃዮቹ ወገኖች መካከል ወ/ሮ ማዓሾ ሃይለ በበኩላቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከመጀመርያው ማታለያ እንጂ አስተማማኝ አልነበረም በማለት  ከበባውና ክልከላው በክንዳቸን እንሰብረዋለን ሲሉም አክለዋል፡፡