—-
በኤርትራ ቴሌቭዥን የተሰራጨውና በሻባይት ድረ ገፅ ለንባብ የበቃው የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን መግለጫ የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ፖሊሲ ጉድለትና ሞኝነት ይበልጥ የታየበት ነው ብሏል።
የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠር የምታራምደው ፖሊሲ ለማጠናከር በምትጥርበት ወቅት ግብኝቱ ጠብ አጫሪነት መሆኑን አመልክቷል።
ጉብኝቱ የአሜሪካ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት በኤሽያ ሲከተለው የቆየ በግድ የለሽነት ላይ የተመሠረተ ፔሌስ ቀጣይነት የሚያሳይ እንደሆነም መግለጫው ያስረዳል ሱዳንና ዝምባቤም የናንሲ ፔሌሲ ጉብኝት ታይዋን የአንዲት ቻይና አካል መሆንዋን በመጥቀስ ጉብኝቱን ተቃውመዋል።
ሶስቱም ሃገሮች ኤርትራ፣ ሱዳንና ዘምባቤ አሜሪካ ለበርካታ ዓመታት የኢኮኖሚ ማዕቀብ ያደረገኘባቸው አገሮች መሆናቸው ይታወቃል።
ኤርትራ ከዚህ በፊት ሩሲያ ዩክሬንን ላይ የፈፀመችውን ወረራ በመደገፍ ብቸኛው የአፍሪካ ሃገር መሆኗ የሚታወቅ ነው።