Home ዜና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ባኖረው ከበባና ክልከላ 30.000 በላይ  የቤት እንስሳት በህክምና እጦት...

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ባኖረው ከበባና ክልከላ 30.000 በላይ  የቤት እንስሳት በህክምና እጦት እንደሞቱ የትግራይ ግብርና  ቢሮ አስታወቀ፡፡

1188

—-

የትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በየዓመቱ ከሃያ ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አውስተዋል፤ በዚህም ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድን የትግራይ ህዝብን ከምደረ-ገፅ ለማጥፋት በማለም በትግራይ ተጠናክሮ የቀጠለዉ ከበባና ክልከላ ተከትሎ በዚህ ዓመት በክትባትና በመድሃኒት እጦት ከሰላሳ ሺ በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት እንደሞቱና ከሁለት መቶ አርባ ሺ በላይ ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ  እንደሚገኙ የትግራይ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ገብሩ ለገሰ ይገልፃሉ፡፡

ዶ/ር ገብሩ ለገሰ የትግራይ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ዳይሬክተር

የእንስሳት ጤና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ገብሩ አክለውም በከባድ ህመም ላይ የሚገኙ የቤት እንስሳቶች እንደ አባሰንጋ/መገረም/፣ ያበደ ዉሻና የመሳሰሉ በቀላሉ ከእንስሳ ወደ ሰዉ ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እየተስፋፋ ነዉ ብለዋል፡፡

በአለም አቀፍ በጎ አድራጊ ድርጅቶች አማካኝነት ወደ ትግራይ የተላከዉ የእንስሳት መድሃኒት ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድን ወደ ትግራይ እንዳይገባ እያደረገ ይገኛል፤ ያሉት ዶ/ር ገብሩ  ይሄ ድርጊት በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የጀኖሳይድ ወንጀል ቀላል ማሳያ ነዉ ይላሉ፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ወደ ትግራይ ምንም ኣይነት መድሃኒት እንዳይገባ   በመከልከሉ በተለምዶ የደስታ ወይንም ኣባሰንጋ እየተባለ የሚጠራው  የእንስሳት በሽታ መባባሱ ተከትሎ በሽታው ከእንስሳ ወደ ሰዎች እየተላለፈ መምጣቱን  እና  በዚህም በርካታ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን   ይታወሳል፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ