—-
VOA የደቡብ ምዕራባዊ ሶማሊያ ባለሥልጣናትን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው ዜና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ሁለት ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮቹን ጌዶ ወደ ተባለ የሶማሊያ ግዛት ማሰማራቱን ዘግቧል።
የጌዶ ግዛት አስተዳደር ቃል አቀባይ ዒሊ የሱፍ ዓብዱላሒ የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሰራዊት ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ መሠማራቱን ገልፀው ለኢትዮጵያ አዋሳኝ በሆነችው የዶላው ከተማና አቅራቢያዋ ካምፕ መመሥረታቸው አስታውቀዋል።
ዓብዱላሒ ዓሊ ጁባም ተብለው የሚጠሩ ቃለ አቀባዩ ለVOA በስልክ እንደተናገሩት ወደ አካባቢው የተሰማራ የፋሽስቱ አብይ ቡድን ሠራዊት ቁጥር ወደ 2000 ይጠጋል።
ዓሊ ጁባ ለሶማሊያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክት ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ አዲስ ችግር መፍጠሩንና ሃይሉ በሂራን ፣ ባኮል እና ጌዶ አካባቢ ስጋት ሆኖ መቀጠሉን ተናግረዋል።
የጌዶ ግዛት ባለሥልጣናት በዚሁ የአልሸባብ አዲስ እንቅስቃሴ ስጋት ላይ መውደቃቸው ቃል አቀባዩ አመላክተዋል።
ይህ ከአፍሪካ ሕብረት ተልእኮ ውጭ ሆኖ ወደ አካባቢው የተሰማራው የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሠራዊት የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚያውቀው ጉዳይ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ጨምረው ገልፀዋል።
የአልሸባብ ሃይል በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ብዙ አካባቢዎች የኢትዮጵያ ደንበርን በመሻገር ሂራንና ባኩል የተባሉ አካባቢዎች ዘልቀው መግባታቸው የፀጥታ ሃይሎችን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።
እንደ አሜሪካ ወታደራዊ ግምገማ የአልሸባብ ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እስከ 150 ኪ.ሜ ዘልቀው ገብተዋል።