—-
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለትግራይ ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች የማቅረብም ሆነ፣ የህዝቦች፣ የእቃና አገልግሎቶች ነፃ እንቅስቃሴ የመፍቀድ ሁኔታ ለድርድር የማይቀርብና ያለምንም መዘግየትና ቅድመ ሁኔተ በመተግበር ግዴታውን ሊወጣ አንደሚገባ አሳሰበ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ም/ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦረል የተረሳው የትግራይ ጦርነት ማብቂያው ጊዜ አሁን ነው በሚል ርእስ በአውሮፓ ህብረት ድረገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ የአምኔስቲ ኢንተርናሽናልና የሂዩማን ራይትስ ወች ሪፖርትን በመጥቀስ እንዳመለከቱት ትግራይ ሁለት አመት እያስቆጠረ ባለው ጦርነት ረሃብና ወሲባዊ ጥቃት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ብዙ ዘግናኝ ግፎች ተፈፅመውባታል ፡፡
መላውን የቀጠናውን አገሮች የማተራመስ አቅም ያለው ይህ ደም አፋሳሹ ጦርነት ማብቂያው ጊዜ አሁን ነው ያሉት ጆሴፍ ቦረል ከቅርብ ሳምንታት በፊት በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የአትሌቲክስ ውድድር የትግራይ አትሌቶች አንፀባራቂ ድል በማስመዝገብ ኢትዮጵያን የተለያዩ ቀለማትን በማልበስ አድምቀዋታል በማለት የአለም ማህበረሰብ በትግራይ ሰቆቃ እያሳለፉ ያሉትን የአትሌቶቹ ቤተሰቦች ትኩረት እንዲደረግባቸው አንዳንዶቸ አጋጣሚውን ተጠቅመውበታል ብለዋል፡፡
በትግራይ አራት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ ጠባቂ መሆኑን ያስረዱት ቦረል እርዳታው ወደ ተረጂዎች ተደራሽ እንዳይሆን አሁንም የነዳጅ እጥረት ዋነኛው ማነቆ ሆኖ መቀጠሉ አስታውቀዋል፡፡
ማዳበሪያም ለአርሶ አደሩ በወቅቱ እንዳልደረሰ ያመለከቱት ጆሴፍ ቦረል በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የፀጥታውን ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስነው ምስራቅ ኢትዮጵያ የአልሸባብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ መግባቱ በአካባቢው የተራዘመ ቀውስ እንደሚያስከትል ምልክት እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ም/ቤት በመጨረሻው ስብሰባው በኢትዮጵየ በድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረስ፣ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን፣ በትግራይ የተሟላ የመሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች መጀመር፣ ወንጀል ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም የአምባገነኑ የሻዕቢያ ሰራዊት ጠቅልሎ ከትግራይ እንዲወጣ ማድረግ ከፋሸስቱ የአብይ ቡድን አጋርነትን እንደገና ለመቀጠል እንደቅድመ ሁኔታዎች የሚቀመጡ ጉዳዮች እንደሆኑ ማመልከቱን የጆሴፍ ቦረል ፅሁፍ ያስረዳል፡፡
ከፋሽሽቱ ቡድን የነበረንን ግንኙነት ከዚህ ቀደም ወደ ነበረበት ለመመለስ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን በቂ ስራ እንዳልተሰራ አመልክቷል ይላል የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ም/ቤት ግምገማ
ባልደረባቸው ኮሚሽነር ሌናርኪክ ባለፈው ሰኔ ወደ ትግራይ መጓዛቸውን ያስታወሱት ጆሴፍ ቦረል የኮሚሽነሩ መልእክት ግልጽ ነበር መሰረታዊ አገልግሎቶች ነፃ የሰዎች፣የእቃና የአገልግሎቶች እንቅስቃሴ የማያወዛግብና ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን ነው ብለዋል ።
ይህን ጉዳይ ህዝብን ከሞት የመታደግ ጉዳይ ነው ፋሸስቱ የአብይ ቡድን ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፣ ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ሂደቱን ለመጀመር አንድ ወገን ቅድመ ሁኔታን የመቀበል ጉዳይ ሳይሆን የአንድን መንግስት ከዜጎች አንጻር ሊወጣው የሚገባ ግዴታ እንደሆነ ነው ያመለከቱት፡፡
ተፋላሚ ወገኖች ስለ ሰላም ማውራታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ድምፅ አልባው ጦርነቱ ግን አሁንም እየቀጠለ ነው ብለዋል ጆሴፍ ቦረል።
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለትግራይ ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች የማቅረብም ሆነ፣ የህዝቦች፣ የእቃና አገልግሎቶች ነፃ እንቅስቃሴን የመፍቀድ ሁኔታ ለድርድር የማይቀርብና ፋሽስቱ ቡድን ያለምንም መዘግየትና ቅድመ ሁኔታ በመተግበር ግዴታውን ሊወጣ አንደሚገባ አሳስበዋል ጆሴፍ ቦረል።