Home Uncategorized ለከፋ ረሃብና ችግር የተጋለጠውን የዋግ-ኽምራ ቢርቢጣ ወረዳ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብለት ጥሪ ቀረበ።

ለከፋ ረሃብና ችግር የተጋለጠውን የዋግ-ኽምራ ቢርቢጣ ወረዳ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብለት ጥሪ ቀረበ።

929

የአገው ህዝብ በልማትም ሆነ በመልካም አስተዳደር ችግር እየተሳቀያ ራሱን በራሱ እንዳያስተዳድር ተከልክሎ የልማት ጥያቄ ማንሳትም እንደ ነውር ተደርጎ ጥያቄ የሚያነሱ ለምን ስለ ዋግ ታነሳላችሁ በማለት በተስፋፊው የኣማራ ሃይል ሲታሰሩና ሲንገላቱ የመጡ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡

 የአገው  ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ተዘግቶ የራሱን ህዝብ በራሱ ልጆች ካለመስተዳደሩ የተነሳ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ የህወሃት ተላላኪ  የሚል ታርጋ ተለጥፎበት የመብት ጥያቄ ለተላላኪ ታረጋ ከማሰጠቱ በላይ ህዝቡ እንደ ወንድም የትግራይ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ በመዝጋት አስርቦ ለመግዛትና ለትምክህተኞች እንዲምበረከክ በማሰብ ሁለንተናዊ ከበባ በማድረግ የምግብ ዋስትናው እንዳያረጋግጥ ታስቦ የተደረገው ለከፋ ረሃብና ችግር አጋልጦት ይገኛል፡፡

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ዘር ለማጥፋት ይሞከራል ተብሎ በማይታሰብበት ግዜ በፋሽሽት አብይ አህመድ ቡድን እና በጄሌዎቹ የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች የአያቶቻቸው ስርኣት ለማስቀጠል በኣገው እና በትግራይ ህዝብ የሰብኣዊ እርዳታ እንዳይገባ በማድረግ ህዝቡ በረሃብ ተሰቃይቶ እንዲያልቅ እየተደረገ ነው ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ ለከፋ ሰው ሰራሽ ረሃብና ችግር ሆን ተብሎ በከበባ ምክንያት ተዘግቶ ለዚህ ዓመት ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ዓመታትም እንደሚራቡና እንዲቸገሩ ታስቦ እየተሰራ ያለ መሆኑን ይህም የሚመለከተው አካል መፍትሄ ካላስቀመጠበት ራሳቸውና ቤተሰቦቻችው ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደተደቀነባቸው ነዋሪዎች ኣክለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአከባቢው ነዋሪዎች በአከባቢው ያለውረሃብ ከምንም በላይ አስከፊ መሆኑ ተረድተው ረጂ ድርጅቶች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲሰጣቸው ተማፅነዋል፡፡  ካልሆነ  ግን ህዝቡ ከረሃብ አልፎ በሂወት የመቆየት ዕድል እንደሌለው ጨምረው አሳስበዋል።

የቢርቢጣ ንኡስ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለፈ ብርሃኑ በበኩላቸው  በፋሽስቱ አብዪ አህመድ መንግስትና በተስፋፊው የአማራ ሃይሎች ስር ሆኖ የተለያዩ መከራና ግፍ ሲደርስበት የመጣው የአገው ህዝብ አሁንም በሰው ሰራሽ ከበባ ምክንያት ህዝቡን ለከፋ ረሃብና ችግር የተጋለጠ መሆኑና ድርጅቶች እርዳታው ወደ ህዝቡ እንዲያደርሱ ብሎም የተራበው ህዝብ ከሞት እንዲታደጉት ሲሉ ጥሪያቸው አቅርቧል።

በሓጋዚ አብረሃ