Home ዜና ሞያሌ ከተማ ሞያሌ ግጭት መቀስቀስ

ሞያሌ ከተማ ሞያሌ ግጭት መቀስቀስ

624

በመንግስት የፀጥታ ሃይሎችና የኦሮሞ ነፃነት ጦር መካከል ግጭት መቀስቀሱ BBC ዘገበ፡፡

BBC የአካባቢውን ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ከጐረቤት ኬንያ በምታዋስነው የንግድ መዳረሻዋ ሞያሌ ከተማ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ አጥቢያ ድረስ የዘለቀ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር፡፡ከመንግስት ሃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ያደረጉት የኦሮሞ ነፃነት ጦር አባላት እንደሆኑ የአካባቢው ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ጦር ኦዲ ታርቢ በትዊተር ገፃቸው እንዳስነበቡት በደቡባዊ ኦሮሚያ መልካ ለሚ በሚባል ሥፍራ የመንግስት ሃይሎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መካለከያ ሠራዊት ከቀናት በፊት በኦሮሞ ነፃነት ጦር የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ነው ሲል በፊስ ቡስ መፃፉ ይሄው የ BBC ዘገባ ያስረዳል፡፡

በዚሁ ፊስ ቡክ ገፅ የመከላከያ ሠራዊት የደቡብ እዝ የኋላ ደጀን አስተባባሪ ኮሌኔል ግርማ አየለን ዋቢ አድርጎ እንደፃፈው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ዓይነት የጦር ማሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ቢቢሲ በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡

ኮሌኔሉ የአካባቢው ማህበረሰብ የኦሮሞ ነፃነት ጦር እኩይ ሴራ በማጋለጥ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በመስጠት በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው ብለው መናገራቸው የዘገበው BBC

በኦነግና በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች መካከል በተለይ በደቡብና ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭት ሲቀስቀስ ይህ የመጀመርያው አይደለም ብሏል BBC በዘገበው’

ከቅርቡ ጊዜያት ወዲህ በኦሮሞ ነፃነት ጦርና በአካባቢው የፀጥታ ሃይሎች እንዲሁም በመከላከያ ሠራዊት መካከል ግጭት ይነሳል ያለው ቢቢሲ መንግስት በኦሮሞ ነፃነት ጦር ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀው ነው ሲል በተለያዩ ጊዚያት ቢገላጥም ታጣቂው ቡድን በበኩሉ በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ላይ ኪሣራ እያስከተለም ነው ይላል ብሎ BBC ዘግቧል’

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት ተጠያቂው የኦሮሞ ነፃነት ጦር እንደሆነ ሲገለፅ መቆየቱ የ BBC ዘገባ ያስረዳል’   በኩኖም ቀለሙ