Home ዜና ረሃብን እንደጦር መሳርያ በመጠቀም በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑ The...

ረሃብን እንደጦር መሳርያ በመጠቀም በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑ The conversation ድረገፅ አስነበበ፡፡

459
0

ረሃብን እንደጦር መሳርያ በመጠቀም በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑ The conversation ድረገፅ አስነበበ፡፡

——

ሰላማዊ ህዝብን በማስራብ  እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም በቀድምት ዘመናት እንደ ወታደራዊ ስልት አገልግሎት ላይ የዋለ  ቢሆንም በአሁኑ ዘመን ይህንኑ ስልት ስራ ላይ በማዋል በትግራይ ህዝብ ላይየጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑን ተገለፀ፡፡

የትግራይ ህዝብ የባንክ አገልግሎት፤ የንግድ እንቅስቃሴዎችና የሰብአዊ  አቅርቦት እንዳይገባ በመከልከል ከሁሉ የከፋ ችግር እንዳጋጠመው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

The conversation የተባለ ድረ ገፅ እንደዘገበው ሰላማዊ  ሰዎችን በማስራብ  ክልክል በሆነው የጥንት ወታደራዊ ስልት በአሁኑ ዘመን ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም  በትግራይ፤ በየመንና ዩክሬን ህዝቦች ላይ እየተፈጸመ ያለው የጀኖሳይድ ወንጀል  ነው፡፡

ዩክሬን ወደ ውጭ ለመላክ አዘጋጅታው የነበረውን  ስንዴና የቅባት እህሎች በሩስያ ወረራ ከተፈፀመባት በኋላ  ምርቷን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ባለመቻልዋ የዓለም አቀፍ የምግብ ግብይት ላይ ቀውስ መፈጠሩን ጠቅሰዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ደግሞ  እንደፈረንጆች  አቆጣጠር በ2021    ማጠናቀቅያ ላይ  በዓለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ህዝብ ከፍተኛ የምግብር እጥረት  እንዳጋጠመው ድረ ገፁ በዘገባው አመላክተዋል፡፡

ሩስያ ረሃብ እንደጦር መሳሪያ መጠቀም ብቻ ሳይሆን  የተጠመደችው ጦርነት በተቀሰቀሰባቸው አገራት ላይ  ከፍተኛ የረሃብ አደጋ እንዲከሰት  ጭምር  አድርጋለች  ብሏል፡፡ በርካታ  መንግስታት ሆን ብለው ረሃብ እንደ ማህበረ-ሰባዊ ማሰቃያ  መንገድ  እየተጠቀሙበት እንደሆነም ዘገባው  አመላክተዋል፡

ድሮ ድሮ ሰላማዊ ህዝብን ማስራብ እንደ ወታደራዊ ስልት መጠቀም እንደጦር ወንጀለኝነት አያስጠይቅም  ያለው ዘገባው በሰብአዊ ቀውስና በምግብ ዋስትና  ላይ ጥናት ያካሄዱ ዓለም አቀፍ የህግ ምሁራን ግን ይህን ዓይነት የወንጀል ተግባር የሚፈፅሙ መንግስታት የምንዋጋበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡

ህዝብን ማስራብ ጊዜው ያለፈበት የጦር መሳሪያ ነው፤ ሮማ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ146 ዓም በወቅቱ ጠላት ብለው የፈረጁትን ሀይል ላይ የውሃ መሰረተ ልማቶችና የሀይል መስመሮች መቁረጥና መዝጋት  ምግብና የእርሻ መሳሪያዎች  ማውደም እንደ ወታደራዊ ስልት  ተጠቅመውበቷል፡፡ ከጊዜ በኋላ ይህንኑ ስልት  መቀየሩን  ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

በቅርብ ጊዜ በተካሄዱ ጦርነቶች ህዝብን በማስራብ ወንጀል ከፈፀሙ መንግስታት መካከል ፋሽስቱ የአብይ ቡድንን ጨምሮ በዩክሬን፤ በማሊ፤ በማይናማር፤  በሶሪያ፤  በየመንና ሌሎች አገራት ስለ መፈፀሙ ማስረጃዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ጦርነት ውስጥ የገቡ ተፋላሚ ሀይሎችም የሰብአዊ እርደታ ሰራተኞችና  ላይ ጥቃት ከመፈፀም በተጨማሪ አርሶ አደሮችን ሀብት የሆኑ እንስሳስት አርደው በመብላትና ጎተራ ውስጥ የሚገኝ ሰብል ማቃጠልና ሌሎች ወንጀሎችን እንደሚፈፅሙ ዘገባው አመላክቷል፡፡

ከ2020 ጀምሮ እስከ 2022 በነበሩ ጦርነቶች  ምክንያት የምግብ እርደታ የሚፈልጉ ህዝቦች ቁጥር ከ99 ሚሊዮን ወደ 166 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች እንዲቋረጡበት ፤ የንግድ እንቅስቃሴው እንዲገታ፤ የሰብአዊ  እርዳታ አቅርቦት ወደ ትግራይ እንዳይገባ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን  ከ19 ወራት በላይ ለዘለቀ ከበባና ክልከላ መዳረጉ ከሁሉም  የተለየ የከፋ ችግር እንደጋጠመው The conversation በዘገባው አመላክቷል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ንብረት በመዝረፍና በማውደም፤ የጅምላ ግድያና ወሲባዊና ፆታዊ ጥቃት በመፈፀም  ለረዥም ጊዜ እንደስልት በመጠቀም የ7 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ኢኮኖሚ እንዲወድቅ ማድረጉንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

ዓለም-አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድቤት በመጥቀስ ዘገባው እንዳመላከተው  ህዝብን በማስራብ እንደጦር መሳሪያ መጠቀም  የሚከለክሉ በርካታ አገራት መኖራቸውን ጠቅሶ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግም ጭምር  ህዝብን የማስራብን ስልት   እንደጦር መሳሪያ መጠቀም  ክልክል መሆኑን አስምሮበታል፡፡

መብራህቱ ይባልህ  

Previous articleየተሰው ጀግኖቻችንን ኣደራና ስእለት በጠንካራ ትግልና መከታ በተተኪ ትውልዶች እያንፀባረቀ ይኖራል!  ዶ/ር ደብረፅየን
Next articleየትግራይ ህዝብ ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ የትግራይ ሴ/  ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው