Home Uncategorized ሰበር የድል ዜና – መስከረም 3, 2015 ዓ/ም

ሰበር የድል ዜና – መስከረም 3, 2015 ዓ/ም

4568

ጠላት የትግራይን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አቅዶ በሁሉም ግንባሮች የጀመረውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በሰራዊታችን የላቀ ፅናት እየተመከተ ይገኛል። 

ጠላት ለወራት የተሟላ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ትግራይን    ዳግም ለመውረር በበርካታ ግንባሮች በዓይነቱ የተለየ ሰፊ ጥቃት ሲሰንዝር ቆይቶ አሁንም ቀጥሎበታል።

ጠላቶቻችን የኢትዮጵያ ሙሉ ሃብት፣ መደበኛና ኢ-መደበኛ ሃይሉን በሙሉ አቅሙ አሰማርቶ የባእድ ወራሪው የኢሳያስ ስርዓትም ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሁለቱም ሀገራት ሁሉን አቀፍ አቅማቸውን በሙሉ አሟጠው በማዝመት የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ሰፊ ዘመቻና ወረራ ሲያካሂዱ ቆይተዋል፤ ይህ በይዘቱና በስፋቱ የተለየ ለ3 ሳምንታት ቀንና ሌሊት የዘለቀው ከባድ ውግያ በጀግናው ሰራዊታችን አስገራሚ ፅናትና ጀግንነት የጠላቶቻችን ሴራ መና አስቀርቶታል።

በዚህ መሰረት ጠላት በደደቢት ግንባር ከ23 ክፍለ-ጦር በላይ እግረኛ ሰራዊት፣  አንድ መካናይዝድ ክፍለ-ጦር፣  3 ክፍለ-ጦር የአማራ ልዩ-ሃይል፣  በጠቅላላ 27 ክፍለ-ጦሮች፣  በሺዎች የሚቆጠሩ ፋኖና ሚሊሻ የሰራዊታችን የመከላከልያ መስመር ሰብረው ወደ ሽሬ ለመግባት ያሰፈሰፈው የጠላት ሃይል ተሽመድምደዋል፤ ጀግናው ሰራዊታችን ለ10 ቀናት ስኬታማ የመከላከል ውግያ ሰያካሄድ ቆይቶ ከመስከረም 1 ቀን 2015 ዓ/ም ወደ ሙሉ የፀረ-ማጥቃት ዘመቻ በመሸጋገር እዛ የነበረው ሃይል ተደምስሰዋል። የተቀረውም  ፈርጥጠዋል።

በአድያቦ ግንባር ከነሃሴ 26፣ 2014 ዓ/ም ጀምሮ በ3 ግንባሮች ማለትም በፋቅያ ገብረ፣ በዋዕላ ንህቢ፣ እና ሕረት ወደ ዓዲ አውዓላ አድርጎ ሽረን ለሞቆጣጠር ያቀደውን 9 የኢትዮጵያ እግረኛ ክፍለ ጦሮች ከ3ሺ በላይ የአማራ ልዩ ሃይልና የሻዕብያ 24 እግረኛ ክፍለ-ጦሮች 2 የመካናይዝድ ክፍለ-ጦር በማሰለፍ ከአስር ቀናት በላይ ሰፊ ጥቃት ሲሰነዝር ቆይተዋል። ጀግናው የትግራይ ሰራዊት የወራሪዎች ጥምር ሃይል በአስተማማኝ ደረጃ ለመስበር እንዲያመቸው ውስን የቦታ ማሻሻያ በማድረግ የመጣውን የጠላት ሃይል በላቀ ብልሃትና ጥበብ በመመከት ሙት፣ ቁስለኛና ሙርከኛ በማድረግ ጠላቶቻችን የጎነጎኑት ሴራ እንዲከሽፍ እያደረገ ይገኛል።

በዓዲ አርቃይ ግንባር ከነሀሴ 28, 2014 ዓ/ም ጀምሮ 6 እግረኛ ክፍለ-ጦሮች፣ አንድ መከናይዝድ ክፍለ-ጦር፣ 3 ክፍለ-ጦር የአማራ ልዩ ሃይል ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሚሊሻና ፋኖ  በማዝመት ርብርብ ሲያደርግ ቆይተዋል።

ጀግናው ሰራዊታችን አሰፍስፎ የመጣው ይሀው ሃይል በተደጋጋሚ እያሽመደመደ ባለበት እንዲቆም አስገድዶታል።

በደቡብ ግንባር ከጳጉሜ 4, 2014 ዓ/ም ጀምሮ የቀጠለው የጠላት ሙከራ 18 እግረኛ  ክፍለ-ጦሮች፣ 4 ክፍለ-ጦር ልዩ ኮማንዶ፣ አንድ ክፍለ-ጦር ሪፐብሊካን ጋርድ፣ አንድ  ክፍለ-ጦር መካናይዝድ፣ 4 ክፍለ-ጦር የአማራ ልዩ ሃይል በሺዎቸ የሚገመቱ ፋኖና ሚልሻ አሰልፎ በወርቄ፣ ጎብዬ፣ ባላጎ፣ ወንዶች በርና አከባቢ አቅጣጫ  ተደጋጋሚ ጥቃት ሲሰነዝር ሰንብተዋል ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ደጋግሞ የመጣውን የጠላት ሃይል በምህረት የለሽ ምቱ በማሽመድመድ ወርቄ፣ አልወሃ፣ ጎብየ እና  ባላጎን አከባቢ  ተቆጣጥሮታል።

በሌላ በኩል በሰቆጣ ግንባር ከነሀሴ 25 – 30, 2014 ዓ/ም የቀጠለው ከ13 በላይ እግረኛ ክፍለ-ጦሮች፣ አንድ የመካናይዝድ ክፍለ-ጦር፣ አራት ክፍለ-ጦር የአማራ ልዩ ሃይል እንዲሁም ብዛት ያለው  ፋኖና ሚልሻ በማዝመት በአበርገለ አድርጎ ሳምረና አከባቢውን ለመቆጣጠር አቅዶ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲያደርግ ቆይተዋል። አሁንም ለመቀጠል እየሰራ ይገኛል፤ ጀግናው ሰራዊታችን ከአገው ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ በመሆን በዚሁ ግንባር የመጣውን ጠላት በመከላከልና በፀረ ማጥቃት እንዲዳከም በማድረግ ጠላት አስታግሶታል።  

ሁሉንም የሚቻልህ ባለ ፅኑ አቋምና እምነት፤  ለትግራይ ህዝብ ማንነትና ህልውና፣ ዋስትና የሆንከው ጀግናው ሰራዊታችን የሰማይና የምድር ሁሉንም ዓይነት የጦር መሳርያ ተጠቅመው የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት የመጡ የሁለት ሀገር ወራሪዎች ሰው ከሚገምተው በላይ ከጠላቶች ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ መሰናክሎችም ሳይበግሩህ በሚያስደንቅ ፅናትና ጀግንነት የጠላት እቅድ እንዲመክን እያደርግክ ትገኛለህ።

በደምህ የትግራይ እናቶች የሃዘን እንባ ሳይሆን የደስታና የኩራት እንባ ይሆናል፤ በመስዋእትነትህ የትግራይ ህዝብና ትግራይ ኮርተውና ተከብረው ይኖራሉ። በምትከፍለው አካላዊ መስዋእትነት  የትግራይ ህፃናትና ታዳጊዎች ይቦርቃሉ። ይህንን እያደረግክ ነውና የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ለምትፈፅመው ገድል ያለውን ክብር በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል።

በፈተናና በጭንቅ ወቅት በማትበገር የሁሉም የፅናትና ጥንካሬ አለኝታ የሆንከው ህዝባችን የአብራክህ ክፋይ የሆነው ጀግናው ሰራዊታችን ይህ ሁሉ ተአምራዊ ገድል ሲፈፅም ሁሉንም ተቋቁመህ ማድረግ ያለብህን አድረገሃል የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ለዚህ ሁሉ ጥረትህ፣  ትግልህ እና ትእግስትህ ያለው ክብርና አድናቆት እየገለፀ ምኞትህንና አደራህን ከዳር ለማድረስ በላቀ ተነሳሽነት እንደምንታገል በዚህ አጋጣሚ ልናረጋግጥልህ እንወዳለን!!

ህልውናችንና ደህንነታችን በክንዳችን

ትግራይ ትስዕር!

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

መስከረም 3, 2015 ዓም

መቐለ