የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ #ስቴፌን ዱጃሪክ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ሰብአዊ እርዳታ ውለማስገባት ከተፈቀደ ጀምሮ 20 የእርዳታ እህል የጫኑ አንድ ነዳጅ የጫነ መኪና ብቻ ወደ ትግራይ መግባታቸው አስረድተዋል፡፡
የፋሽስት አብይ ቡዱን ወደ ትግራይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባበ ሚል በጊዜያዊነት ግጭትን የማቆም ውሳኔ ካስተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ 16 ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን ትርጉም ያለው ለውጥ ሊታይ አለ መቻሉን ከትግራይ መንግስት እስከ #የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጨምሮ ያሉት አካላት በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
ውሳኔውን ተከትሎ ለጋሽ ድርጅቶች በየቀኑ ከ100 ያላነሱ የርእዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ለማስገባት ተስፋ ቢያሳድሩም የፋሽስቱ ቡዱንና ሸሪኮቹ እየፈጠሩት ባለውሰን ካላምክንያት አሁንም ለትግራይ ህዝብ ሊደርሱ ለትአለመቻላቸው ገልፀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አጋሮቹ መጋቢት 20 እና 21 የእርዳታ እህል ከጫኑት 20 መኪኖችና ነዳጅ ከጫነ አንድ መኪና በስተቀር ወደ ትግራይ የገባምንም እንደሌለና የህምና ካለፈው ታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የእርዳታ እህል በመኪና የገባ አለመኖሩን ማረጋገጣቸው ኣስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በትግራይ ባለው የሰብአዊ እርዳ ታአቅርቦት እጥረት ተከትሎ ለሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ከባድ ፈተና እየሆነባቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
በዋነኛነትም የባንክ፣የመብራትና የስልክ አገልግሎት ባለ መኖሩ ከህዝቡ አልፎ ለእርዳታ ሰራተኞችም አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑን ስቴፈን አመልክተዋል፡፡
በየስድስት ሳምንንት አምስት ነጥብ ሁለት ሚልዮን የትግራይ ህዝብ የእርዳታ እህል ያስፈልገዋል ያሉት ስቴፈን ሆኖም ባለፉት ስድስት ወራት ለአንድ ነጥብ ሁለት ሚልዮን ለሚሆን ህዝብ የአንድ ጊዜ እርዳታ ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ከመግባታቸው በፊት በመጋዘኖች ምንም አይነት የእርዳታ እህል ባለመኖሩ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር የትግራይ ህዝብ ለረሃብ መጋለጡን ለማረጋገጥ መቻላቸው አስረድተዋል ቃልአቀባዩ ፡፡
በመጋዘን ውስጥ እህል የሚባል ነገር ስላ ልነበረ ለህዝቡ የእርዳታ እህል ማቅረብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ይህንኑ ተከትሎም ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ሚልዮን የህክምና አገልግሎት ማግኘት ከሚፈልጉ አጋሮቻችን የደረሱላቸው 27 ሺህ ለሚሆኑት ብቻ ናቸው ብለዋል ስቴፈን ዱጃሪክ፡፡
የፋሽስቱ ቡዱን የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ለማስገባት እንዲቻል የወሰነውን ግጭትን በጊዜያዊነት የማቆም ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የትግራይ መንግስት በሙሉ ፈቃደኝነት መቀበሉ ይታወሳል፡፡
ሆኖም እስካሁን የሰብአዊ እርዳተውን በሚገባ ወደ ትግራይ እየተላከ እንደሆነና ሌሎች አገልግሎቶችም እንደተጀመሩ ተደርጎ በፋሽስቱ አመራሮች ሲሰራ ጩየቆዩት መረጃዎች ከእውነት የራቁና የአለም ማህበረሰብ ለማደናገር የሚደረጉ ጥረቶች ብቻ መሆናቸው የትግራይ መንግስት መግለፁ ይታወሳል፡፡
ተካ ጉግሳ